አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት
ለካናዳ የስራ ስምሪት ምንም አይነት ይፋዊ ምዝገባ አለመጀመሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳስታወቀው የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ወይም AI/Deepfake በመጠቀም የተፈበረኩና አሳሳች ምስሎችንና በቪዲዮዎችን በማሰራጨት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወደ ካናዳ “ምዝገባ ጀምሯል” የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን በመልቀቅ ማህበረሰቡን በማደናገር የሚገኙ አካላት መኖራቸውን አስታውቋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል እና ከካናዳ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ዜጎችን አሰልጥኖ ወደ ካናዳ ለመላክ የሚያስችል ስምምነት ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም መፈራረሙ ይታወሳል።ይህንኑ ተከትሎ፣ አንዳንድ ሕገ-ወጥ አካላት የፈጠራ ወሬዎች በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ የሚገኙ ሲሆን በሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI/Deepfake) በመጠቀም የተፈበረኩና አሳሳች ምስሎችንና በቪዲዮ በማሰራጨት “ምዝገባ ተጀምሯል” የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን በመልቀቅ ማህበረሰቡን ማደናገር ላይ ይገኛሉ።
በግል ስልክ ቁጥሮች ደውሉ በማለት ዜጎችን ለኢኮኖሚያዊ ብዝበዛ መጋበዝ ላይ ሲሆኑ እነዚህ ማስታወቂያዎች ሙሉ በሙሉ የማጭበርበር ተግባራት መሆናቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማስጠንቀቁን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡በአሁኑ ወቅት ለካናዳ የሥራ ስምሪት ምንም አይነት ይፋዊ ምዝገባ አልተጀመረም፡፡
በግል ስልክ ቁጥሮች የሚደረጉ ጥሪዎችም ሆኑ የሚላኩ አጫጭር መልዕክቶች ሚኒስቴሩን መስሪያ ቤቱን እንደማይወክሉ ያስታወቀው ቢሮው የምዝገባ ጥሪ የሚደረገው በብሔራዊ ቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች፤ የሚኒስቴሩን ይፋዊ የማረጋገጫ ምልክት ባላቸው ማህበራዊ ትስስር ገጾች ብቻ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.