ልጅነት በቤተሰብ ሕግ እንዴት ይረጋገጣል?

- Advertisement -
Sidebar AD

በኢትዮጵያ ሕግ ማእቀፍ

ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው

መግቢያ
#Ethiopia | በዚህ ጽሁፍ አንድ ሰው ከወላጅ አባቱ ወይም እናቱ ልጅነትን እንዴትና በምን በምን መንገድ እንደሚያረጋግጥ የፌደራል የተሻሻለው የቤተሰብ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ህግን መሠረት በማድረግ ለአንባቢያን የህግ ግንዛቤውን ከፍ በማድረግ ለፍትህ ስረአቱ ገንቢ ይሆን ዘንድ ይህን ጽሁፍ አዘጋጅተን ለእናንተ አቅርበናል።

1. ልጅነት በምን በምን መንገድ ይረጋገጣል?

1.1 በልደት ምስክር ወረቀት

ልጅነት የሚረጋገጥበት የመጀመሪያው መንገድ በልደት ምስክር ወረቀት ነው። በልደት ምስክር ወረቀቱ ላይ አንድ ሰው የዚያ ሰው ልጅ የሚገልጽ ከሆነ የዚያ ሰው ልጅ እንደሆነ ደተርጎ የሚታሰብ ሲሆን ይህ በፌደራል የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 154 ላይ ተደንግጎ የተቀመጠ ነው።

1.2 በልጅነት ሁኔታ

ይህ የልጅነት ማረጋገጫ መንገድ የልደት ምስክር በሌለ ጊዜ የሚረጋገጥበት ነው። የልጅነት ሁኔታ ማለት አንድ ልጅ ከወላጆቹ ጋር ያለው ግንኙነት እንደ ልጅ እና ወላጅ ግንኙነት የሆነ እና በሚኖርበት ማህበረሰብ ዘንድ የልጅ እና ወላጅ(አባት ወይም እናት) ግንኙነታቸውን ተቀባይነት ያለው ሆኖ ሲገኝ ነው ፤የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 156 በዚህ ጊዜ ፍርድ ቤት የህግ ግምት በመውሰድ ልጅ ነው ሲል ውሳኔ ይሰጣል። 157 /1/ይሁን እንጂ በሌላ አካል በማስረዳት ሊፈርስ ይችላል። 157/2/

1.3 በፍርድ ቤት ተወላጅነት ማረጋገጥ

ይህ የልጅነት ሁኔታ በሌለ ጊዜ በሌሎች በማናቸውም ከተጨባጭነት የልጅነት እና ወላጅነት ግንኙነትን የሚመነጩ ምልክቶችን በሚገልጹ ማስረጃዎች ሊረጋገጡ ይችላሉ። እነዚህም ማስረጃዎች የሰው የሰነድ ፣የፎቶ ፣የድምጽ፣ምስለ እንቅሰቃሴ/ቪዲዮ/ ወይም/እና/ ሌሎች ማስረጃዎች ሊሆኑ ይችላሉ። አንቀጽ 158/1/ በእነዚህ ማስረጃ መሠረት ፍርድ ቤት ልጅ ተወላጅነትን ሊያረጋግጥ ይችላል።

ይሁን እንጂ የተወላጅነት ክስ ከትዳር ሁኔታ ውጭ በፍርድ ቤት በማስረጃ ክስ ለማቅረብ መጀመሪያ ፍርድ ቤቱ መፍቀድ አለበት። 158/3/ የሚፈቅደውም ተወላጁ ተጨባጭነት ካላቸው ግምቶች ወይም ምልክቶች በመነነሳት ነው።

2. ተወላጅነት ክስ በማን ሊቀርብ ይችላል ?

ክስ የሚቀርበው ቀልጁ፣በአሳዳሪ ወይም በወራሾቹ ሲሆን የልጁ እናቱም ሆነ አባቱ ማቅረብ ይችላሉ። አንቀጽ 160

3. በተወላጅነት ላይ ተከሳሽ ማን ሊሆን ይችላል?

ተወላጅነትን ለማረጋገጥ ክሱን ያቀረበችው እናት ነኝ በምትለው ሲሆን ክሱ የሚቀርበው በልጁ ላይ ነው። ክሱ የቀረበው በሌላ ሰው ሲሆን ተከሰሽ የሚሆነው ወራሾች ወይም የልጁ እናት ትሆናለች።

4. ማጠቃለያ እና የህግ ምክር

ልጅነት የሚረጋገጠው በልደት ሰርተፍኬት፣በልጅ ሁኔታ ወይም በተወላጅነት በማናቸውም በሚቀርቡ ማስረጃዎች ሲሆን ልጅነት በጉልህ ከሁሉም በይበልጥ የሚያስረዳው የልደት ምስክር ወረቀት በመሆኑ ማናቸውም ዜጎች የልደት ምስክር ወረቀት መያዛቸው ፍርድ ቤት ከመሄድ እና በማስረጃ ለማረጋገጥ ከሚያስለፋ ድካም የሚያድን ሲሆን በፍርድ ቤት በትዳር ሁኔታ እና በማስረጃ በተወላጅነት የሚረጋገጠው ሊፈርስ እና ሊስተባበል የሚችል ነው።

ማጣቀሻ/Reference/
የፌደራል የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992
ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
0929101037,0983337690


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2