“ኢትዮጵያ ከምታስቡት በላይ እየተገነባች ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
👉🏼 ዜጎች መልካም ነገሮችን በማየት ተስፈኛ ሊሆኑ ይገባልም ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ብዙዎች ከሚያስቡት በላይ በጠንካራ መሠረት ላይ እየተገነባች መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ በገጠመበትና ትልልቅ የዓለም አየር መንገዶች በረራዎቻቸውን እያቋረጡ ባሉበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሳይገታ መቀጠሉን ጠቅሰዋል።
ይህም የሆነው መንግሥት ለነዳጅ ድጎማ በወር እስከ 20 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ወጪ በማውጣቱና ሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ ባደረገው ከፍተኛ ጥረት መሆኑን አስረድተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ ዜጎች መልካም ነገሮችን በማየት ተስፈኛ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
“ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የነበረው 27 ሚሊዮን ተረጂ ቁጥር አሁን ላይ ወደ 3 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱ ትልቅ ስኬት” መሆኑን ጠቁመው፣ እንዲህ ያሉ ሀገራዊ ድሎች በተራ ዜና ብቻ መታለፍ እንደሌለባቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችው የልማትና የግንባታ ጉዞ ለተነሱት ጥያቄዎች ሁሉ ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠ መሆኑንና ይህም የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አጽንኦት ሰጥተውበታል።
@seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.