የመድፈኞቹ እና የረድዮ ብላንኮዎቹ የዛሬ ምሽት ብርቱ የሜዳ ላይ ፍልሚያ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአውሮፓ መድረክ ታላቅ ግምት የሚሰጠው የአርሰናል እና የአትሌቲኮ ማድሪድ የዛሬ ምሽት ጨዋታ የተለያዩ የጨዋታ ፍልስፍናዎች የሚጋጩበት በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

መድፈኞቹ በፈጣን የማጥቃት እና የኳስ ቁጥጥር የበላይነት ላይ ትኩረት ሲያደርጉ፣ በአንጻሩ አትሌቲኮ ማድሪዶች በጠንካራ መከላከል እና በመልሶ ማጥቃት ብቃታቸው የሚታወቁ በመሆናቸው ጨዋታው የታክቲክ ቼዝ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

አትሌቲኮ ማድሪድ በገዛ ሜዳው እና በደጋፊዎቹ ፊት እጅግ ፈታኝ ቡድን መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሚኬል አርቴታ ይህንን ተረድቶ ዛሬ ምሽት ከከፍተኛ ማጥቃት ይልቅ ጥንቃቄ የተሞላበት የኳስ ቁጥጥርን ምርጫው ሊያደርግ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

ዲዬጎ ሲሚዮኒ ቡድናቸው መጀመሪያ ግብ እንዳያስተናግድ አድርገው በማደራጀት በአንድ አጋጣሚ መርቶ ለመውጣት የሚጠቀሙበት የቆየ ታክቲክ በመኖሩ አርሰናል በከፍተኛ ትዕግስት መጫወት ይኖርበታል፡፡

የስፖርት ተንታኞች እንደሚጠቁሙት አርሰናል በአትሌቲኮ ተጫዋቾች ግፊት እና ጨዋታን የማጓተት ስልት ሳይበሳጭ በረጋ መንፈስ መጫወት ይኖርበታል፡፡

መድፈኞቹ ዛሬ ምሽት ቢያንስ አንድ የሜዳ ውጪ ግብ ማስቆጠር ከቻሉ በለንደኑ ኤምሬትስ ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ ትልቅ እፎይታ ይሆንላቸዋል፡፡

በተለይም የተከላካይ መስመር ተሰላፊዎቹ ሳሊባ እና ጋብሪኤል የአትሌቲኮን አጥቂዎች መቋቋም ከቻሉ፣ አርሰናል በሜዳው ውጤቱን የመቀልበስ እና ስህተቶቹን የማረም ሰፊ እድል ይኖረዋል፡፡

አለባቸው ደሳለኝ
ከለንደን 🇬🇧

#አርሰናል #አትሌቲኮማድሪድ #ቻምፒዮንስሊግ #ስፖርት #እግርኳስ #መድፈኞቹ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: