የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር ያለው አባተ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተከናወነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባኤ የነበሩት የአምባሳደር ያለው አባተ ረታ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ተፈጽሟል።

በዚህ የመጨረሻ የስንብት መርሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ቤተሰቦቻቸው ተገኝተው ሽኝት አድርገውላቸዋል።

አምባሳደር ያለው አባተ በመጋቢት 10 ቀን 1946 ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር ቆቦ ወረዳ ጉብዬ ከተማ የተወለዱ ሲሆን ትምህርታቸውን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት አጠናቀዋል።

በሥራ ዘመናቸውም ከአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት ጀምሮ በተለያዩ የክልልና የፌዴራል የኃላፊነት እርከኖች ላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል።

በተለይም በፌዴሬሽን ምክር ቤት በአፈ ጉባኤነት እንዲሁም በብራዚል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን የዲፕሎማሲ ሥራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል።

ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በሕክምና ሲረዱ የቆዩት አምባሳደሩ በ72 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

#አምባሳደርያለውአባተ #ኢትዮጵያ #ዜና #መረጃ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2