የዞን 5 የአይ ኤች ኤፍ ትሮፊ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​የዓለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን (IHF) የዞን 5 የምስራቅ አፍሪካ ትሮፊ ውድድር ከፊታችን ሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 10 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሁለት የዕድሜ እርከኖች ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።

​የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት እንደገለጹት ዝግጅቱ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን እና በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። ውድድሩ ከ17 ዓመት በታች (Youth) እና ከ19 ዓመት በታች (Junior) የዕድሜ ክልሎችን ያካተተ ሲሆን፣ አሸናፊዎቹ በቀጥታ የአህጉራዊው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናሉ።

​በታላቁ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆኑት ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ታንዛኒያ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሱዳን ናቸው።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: