#Ethiopia | ስዊድናዊው የፊት መስመር ተሰላፊ ቪክቶር ዮኬሬሽ ወደ ሰሜን ለንደን ካመራ በኋላ ያለው ቆይታ በብዙዎች ዘንድ የሁለት ተቃራኒ ስሜቶች መድረክ ሆኗል። ዮኬሬሽ በአርሰናል ቤት የመጀመሪያ የውድድር ዓመቱን እያጠናቀቀ ቢሆንም፣ የደጋፊዎችን የ “ጨራሽ አጥቂ” ጥማት ሙሉ በሙሉ ሊያረካ አልቻለም በሚል ስጋቶች ሲነሱበት ቆይቷል።
ምንም እንኳን ተጫዋቹ በሁሉም ውድድሮች 18 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ቢችልም፣ ከአንድ ትልቅ የዝውውር ዋጋ እና ተስፋ አንፃር ቁጥሩ አሁንም አጠያያቂ ሆኖበታል።
በተለይም በሻምፒዮንስ ሊጉ ካስቆጠራቸው 4 ግቦች መካከል ሁለቱ በአትሌቲኮ ማድሪድ ላይ የተቆጠሩ መሆናቸው፣ በትልልቅ መድረኮች ላይ ያለውን ወጥ አቋም ጥያቄ ውስጥ ጥሎት ነበር።
በቅርብ ሳምንታት የቋሚነት ቦታውን ለሀቨርትዝ አሳልፎ የሰጠው ዮኬሬሽ፣ የጀርመናዊው ኮከብ መጎዳትን ተከትሎ ዛሬ ምሽት ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል።
ሚኬል አርቴታ በአጥቂ መስመር ላይ ካላቸው ውስን አማራጮች አንጻር፣ እምነታቸውን በዮኬሬሽ ላይ ለመጣል ተገደዋል።
ይህ ጨዋታ ለዮኬሬሽ ግቦችን ከማስቆጠር ባለፈ፣ በቀዝቃዛ አጀማመር የጀመረውን የአርሰናል ቆይታ ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ትልቅ አጋጣሚ ነው።
ዮኬሬሽ ዛሬ ምሽት በሚያሳየው ብቃት የደጋፊዎቹን ልብ መልሶ ማግኘት ይችል ይሆን? ወይስ አሁንም የ “ጨራሽ አጥቂ” ፍለጋው ይቀጥላል? የሚለው በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#Arsenal #ViktorGyokeres #PremierLeague #ChampionsLeague #Arteta #FootballNews #Gunners #SwedenStriker
Source: GetuTemesgen









No comments yet.