ሰሜን ኮርያ የጎረቤቷን የደቡብ ኮርያን ድራማዎችን የተመለከቱ ሰዎችን በሞት መቅጣት መቀጠሏ ተሰማበሰሜን ኮሪያ የኮቪድ-19 ወረ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ሰሜን ኮርያ የጎረቤቷን የደቡብ ኮርያን ድራማዎችን የተመለከቱ ሰዎችን በሞት መቅጣት መቀጠሏ ተሰማ
በሰሜን ኮሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የሞት ቅጣት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ሲል ሴኡል ላይ የተመሰረተዉ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ገልጿል።ከጃንዋሪ 2020 እስከ 2024 መጨረሻ ድረስ ቢያንስ 153 ሰዎች ተገድለዋል ወይም ሞት ተፈርዶባቸዋል፡፡ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት በነበሩት አምስት ዓመታት ውስጥ 44 ሰዎች ተቀጥተዉ እንደነበረ የሽግግር ፍትህ የስራ ቡድን አስታዉቋል።
በጣም ከተለመዱት ጥፋቶች መካከል አንዳንዶቹ ከሃይማኖት፣ ከአጉል እምነት እና ከውጪ የባህል ይዘት ጋር የተያያዙ ሲሆን የደቡብ ኮርያ ድራማዎን መመልከት ለቅጣቱ ምክንያት ሆኗል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2015 እስከ በ 2019 መካከል ባሉት ዓመታት የሞት ቅጣት ቁጥሩ ቀንሶ ነበር፡፡ ለመቀነሱም ዋና ምክንያቱ ዓለም አቀፍ ጫናዎች የመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄን ተከትሎ ነዉ። ነገር ግን ፒዮንግያንግ ድንበሯን ከዘጋች በኋላ በ2020 ግድያ ጨምሯል ሲል የሽግግር ፍትህ የስራ ቡድን አስታዉቋል።
መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት በሰሜን ኮሪያ በኪም የግዛት ዘመን መጀመሪያ ላይ የሞት ፍርድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና በ2013 ከ80 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ሲል አስታዉሷል።ፒዮንግያንግ ስልታዊ በሆነ መንገድ የሰብአዊ መብት ረገጣ እየፈፀመች መሆኑን ያረጋገጠውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባደረገው ጥናት መሰረት ቁጥሩ እየቀነሰ የመጣ ይመስላል።በ2020 ግን ቢያንስ 54 ሰዎች ተገድለዋል ፣በ2021 ደግሞ 45 ሰዎች ሲገደሉ በአንድ ዓመት ከፍተኛ አመዘጋገብ የተፈጸመበት ነዉ፡፡
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: