ለምሁር ገዳመ ኢየሱስ
የቤተክርስቲያን የምርቃት ጉዞ
#Ethiopia | ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይም በጉራጌ ዞን ወንጌልን በማስፋፋት ባዕድ አምልኮን ያስወገዱ ታላቅ ሐዋርያ ናቸው።
ጻድቁ ማዕከላቸውን በምሁር ኢየሱስ ገዳም በማድረግ በምሁርና በአካባቢው 156 አብያተ ክርስቲያናትን በመትከል ለቤተ ጉራጌ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እድገት መሠረት ጥለዋል።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዓይ የገዳሙን ጥንታዊነትና ቅድስና ተረድተው ገዳሙን ለማቅናት የነበራቸው ምኞት በደቀ መዝሙራቸው በብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ አማካኝነት እውን ሆኗል።
አቡነ መልከ ጼዴቅ በምሁር ኢየሱስ አካባቢ ተወልደው በዝዋይ ገዳም ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ቤተክርስቲያንን በታማኝነት አገልግለዋል።
የጉራጌ፣ ከንባታና ሀድያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተሾሙ በኋላም መንፈሳዊ አባታቸው አቡነ ጎርጎርዮስ በምሁር ገዳም ላይ የነበራቸውን ራእይ በተግባር ቀይረዋል።
ብፁዕነታቸው በእግር፣ በበቅሎና በመኪና ተጉዘው በአቡነ ዜና ማርቆስ የተተከሉ አብያተ ክርስቲያናትን በማነቃቃት የአብነትና የአዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲቋቋሙ አድርገዋል።
ገዳሙ በኢኮኖሚ ራሱን እንዲችል በአዲስ አበባ፣ በወልቂጤና በሐዋርያት ከተማ ገቢ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶችን ከመጀመራቸውም በላይ የአሁን ሕንጻ ቤተክርስቲያን መሠረት ጥለዋል።
ብፁዕነታቸው በ50 ዓመታቸው ሰኔ 14 ቀን 2002 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም የጀመሩት ሥራ ዛሬም ፍሬ እያፈራ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል የጉራጌ ሀገረ ስብከትን እየመሩ ያሉት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሣልሳይ፣ ቀደምት አባቶች የጀመሩትን የሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ ተጠናቋል
መላው ሕዝበ ክርስቲያን
ሚያዝያ 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም
እንዲገኝ ጥሪ አቅርበዋል።
አዘጋጅ ምሁር ገዳም ኢየሱስ
ለመመዝገብ በስልክ ቁጥር
0910015981
0913383033 / 0911083713 ይደውሉ
#ምሁር_ኢየሱስ #አቡነ_ዜና_ማርቆስ #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ጉራጌ #መነኩሴ #ቤተክርስቲያን #መንፈሳዊ #ታሪክ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen









No comments yet.