በ’ቢልለኔ ስዩም
#Ethiopia | አንድ ሊትር ናፍጣ ኢትዮጵያ ውስጥ 1 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው
– አንድ ሊትር ቤንዚን ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ 0.90 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው
በአንጻሩ በአጎራባች ሀገራት የሁለቱም የነዳጅ ዓይነቶች አማካይ ዋጋ 1.50 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው።
ሀገራችን ሙሉ በሙሉ (100%) የነዳጅ ፍላጎቷን በገቢ ምርት የምታሟላ ሲሆን፣ በዋነኛነት የምታስገባበት ምንጮቿም የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ናቸው።
*[ኢትዮጵያ ነዳጅ በዝቅተኛ ዋጋ የምታቀርበው ለምንድነው?]*
መልሱ የመንግስት ድጎማ ነው።
ኢትዮጵያ ወደ 130 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያላት ሀገር ናት። ዜጎችን ከዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት ለመጠበቅ መንግስት የነዳጅ ወጪን ከፍተኛውን ክፍል ይሸፍናል።
1. መንግስት በአሁኑ ወቅት መደበኛ ከሚደጉመው በተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር በየወሩ ለነዳጅ ድጎማ እያደረገ ይገኛል፤
2. ይህም የዓለም የነዳጅ ዋጋ በሚጨምርበት ወቅትም በሀገር ውስጥ ያለው ዋጋ እንዳይንር ለማድረግ የተወሰነ ውሳኔ ነው።
*[በመካከለኛው ምስራቅ ምን እየተከናወነ ነውወቅትም
ወደ 20% የሚጠጋው የዓለም የነዳጅ እና የጋዝ ምርት የሆርሙዝ ሰርጥ ተብሎ በሚጠራው ወሳኝ የባህር መስመር በኩል ያልፋል። ይህ መስመር ለኢትዮጵያ እጅግ ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም ሀገሪቱ የምታስገባው ነዳጅ እና የናፍጣ ጭነት በዚህ መስመር የሚያልፍ በመሆኑ ነው።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከማርች 2 ቀን 2026 ጀምሮ በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ግጭት ምክንያት፦
– የሆርሙዝ ሰርጥ ለንግድ መርከቦች ዝግ ሆኖ ቆይቷል፤
– በዚህም ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ታዝዞ ሊመጣ የነበረ ከ180,000 ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ዘግይቷል፤
– አብዛኛዎቹ አቅራቢዎችም በቀውሱ ምክንያት ነዳጅ ማቅረብ አቁመዋል፤ የነዳጅ ማጣሪያዎችም ስለተጎዱ አቅርቦት ቀንሷል።
*[የኢትዮጵያ መንግሥት ምን አይነት እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል?]*
1. የትራንስፖርት፣ የግብርና እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ስራ ለማስቀጠል የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ከተነሳበት ወቅት ጀምሮ በቀን 4.5 ሚሊዮን ሊትር ገደማ ናፍጣ ሲያቀርብ ቆይቷል።
2. የሆርሙዝ ሰርጥ አሁንም ዝግ ሆኖ ባለበት ወቅት፣ ዜጎች ለእንግልት እንዳይዳረጉ እና ምርታማነት እንዳይጓደል፣ በዛሬው ዕለትም የናፍጣ አቅርቦት ከቅድመ ጦርነት ወደ ነበረው የአቅርቦት መጠን 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ ተወስኗል።
3. የሀገራችንን እና የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት መንግሥት ነዳጅን በከፍተኛ የዓለም ገበያ ዋጋ ከተለያዩ አማራጭ አቅራቢዎች እየገዛ ነው።
4. ነዳጅን አስቀድሞ ከተያዙ ጭነቶች ከመጠበቅ ይልቅ፣ ፈጣን አቅርቦት ለማግኘት በዕለቱ የገበያ ዋጋ ወዲያውኑ የመግዛት ስልትን (spot purchasing) እየተጠቀመ ነው።
5. ከመደበኛው ዋጋ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን በመሸፈን የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን ቀጥሏል።
6. ምንም እንኳን መዘግየቶች እና ረጅም ሰልፎች ቢኖሩም፣ ሌሎች ሀገራት ማደያዎችን እየዘጉ እንዲሁም የነዳጅ ቁጠባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እያወጁ ባሉበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ነዳጅ አሁንም ባጠቃላይ ወደ ሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ማደያዎች እንዲቀርብ እያደረገ ይገኛል።
ናፍጣ በሀገሪቱ ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል የነዳጅ ዓይነት በመሆኑ ከፍተኛ ፍላጎት የሚታይበት እና በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ምክንያት ለእጥረት የተጋለጠ ሲሆን፤ የቤንዚን አቅርቦት ግን በአንፃራዊነት የተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
*[በመካከለኛው ምስራቅ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት መቆራረጥ ጉዳዩ እስኪሰክን ዜጎች ምን ማድረግ ይችላሉ?]*
– ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን በመለየት፣ ሁኔታውን መረዳትና መንግስት ከጎናችሁ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው።
– ከሀሰተኛ ወሬዎች እና ከተሳሳቱ መረጃዎች ራስዎን ይጠብቁ
– አጋጣሚውን በመጠቀም ለማትረፍ የሚሞክሩትን ያጋልጡ
– አሁን ያለውን የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ በመገንዘብ በትዕግስት እና በጥንካሬ ለማለፍ ይሞክሩ
– አላስፈላጊ ጉዞዎችን በመቀነስ ነዳጅንና ሌሎች ውስን ሀብቶችን በጥንቃቄ ይጠቀሙ።
ምንም እንኳን ትልልቅ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች ቢኖሩብንም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ አቅርቦት እንዳይቋረጥና ዜጎችን ከእንግልት ለመከላከል አተኩሮ እየሰራ ነው።
በትብብር እና በትዕግስት ይህንን አስቸጋሪና ተለዋዋጭ የዓለም አቀፍ ሁኔታ፤ በጋራ ማለፍ እንችላለን!
#Ethiopia 🇪🇹
Source: GetuTemesgen









No comments yet.