ዜና እረፍት፦ ታዋቂዋ የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቦኒ (Boni) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየችበቲክቶክ እና በፌስቡክ መድረኮች በ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ዜና እረፍት፦ ታዋቂዋ የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቦኒ (Boni) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
በቲክቶክ እና በፌስቡክ መድረኮች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ማፍራት የቻለችው ወጣት ቦኒ (Boni) ህይወቷ ማለፉ ተሰማ።
ቦኒ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ስራዎቿ የምትታወቅ ሲሆን፣ በቲክቶክ ከ823 ሺህ በላይ እንዲሁም በፌስቡክ ገጿ ከ298 ሺህ በላይ ተከታዮች ነበሯት።
ወጣቷ ከዚህ ዓለም ከመለየቷ በፊት ባስተላለፈችው የመጨረሻ መልዕክት፤ በህይወት ጉዞዋ ውስጥ የገጠሟትን ተግዳሮቶች በማንሳት ለተከታዮቿ እና ለሚወዷት ሰዎች በሙሉ ስንብቷን ገልጻለች።
በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰነዘሩ አሉታዊ አስተያየቶች እና የቃላት ጥቃቶች በሰዎች የአእምሮ ጤና ላይ የሚያሳድሩት ጫና ከፍተኛ መሆኑን ይህ ክስተት ዳግም አሳስቧል።
የብዙዎችን ቀልብ የሳበው የመጨረሻ መልዕክቷም፦ “ለሁላችሁም ይቅርታ አድርጌያለሁ፣ እናንተም ይቅር በሉኝ” የሚል ይዘት ነበረው።
ይህ አሳዛኝ ክስተት ሁላችንም በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን ላይ እንድንጠነቀቅ እና ለሰዎች የምንሰጠው አስተያየት በህይወታቸው ላይ የሚያመጣውን ለውጥ እንድንገነዘብ ያደርጋል።
ለቤተሰቦቿ፣ ለቅርብ ወዳጆቿ እና ለተከታዮቿ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።#ጉርሻ
ነፍስ ይማር!
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1