የሟች እህቱን አስከሬን ወደ ባንክ ይዞ የሄደው አነጋጋሪ ግለሰብ
በህንድ አንድ ግለሰብ የሟች እህቱን አስከሬን ከመቃብር አውጥቶ ወደ ባንክ ይዞ በመሄዱ በመላው አለም መነጋገሪያ ሆኗል።
ግለሰቡ ይህንን ለማድረግ የተገደደው የእህቱን የባንክ ሂሳብ ለማንቀሳቀስ ባደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ በባንኩ ሰራተኞች “ባለቤቷ በአካል መቅረብ አለባት” የሚል ምላሽ በመሰጠቱ እንደሆነ ተነግሯል።
እንደ ‘ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ’ ዘገባ ከሆነ፣ ግለሰቡ እህቱ መሞቷን ለባንኩ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ቢያሳውቅም፣ ባንኩ ግን የሟችን የባንክ ሂሳብ ለመልቀቅ የሂሳቡ ባለቤት በአካል መገኘት አለባት የሚል ግትር አቋም ይዞ ቆይቷል። ለወራት የቆየው ይህ ውዝግብ
ግለሰቡ የሟች እህቱን አስከሬን ቆፍሮ በማውጣት በቀጥታ ወደ ባንክ ቅርንጫፍ በመውሰድ እህቱ መሞቷን በተግባር ለማሳየት መሞከሩ ተገልጿል።
ድርጊቱ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ ብዙዎች ባንኩ ለፈጸመው “ኢ-ሰብአዊ” አሰራር ተጠያቂ መሆን አለበት እያሉ ይገኛሉ። ባንኩ በበኩሉ ስለ ሁኔታው በዝርዝር የሰጠው ምላሽ እንደሌለ ዘገባው ያስረዳል።
@seledadotio

No comments yet.