#Ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው አለመረጋጋት ሳቢያ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ የተፈጠረው የዋጋ ንረት እና የአቅርቦት መስተጓጎል በሀገራችን የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ጫና አሳድሮ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ይህ ዓለም አቀፋዊ ችግር በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦትን በግማሽ በመቀነስ በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ መስተጓጎል ፈጥሮ ነበር፡፡
መንግስት የችግሩን አስከፊነት ለመቀነስ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ የሎጂስቲክስና የአቅርቦት ማስተካከያ እርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡
እነዚህ እርምጃዎች በዋናነት የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅና የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚው እንዳይናጋ ለማድረግ የታለሙ ናቸው፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው ይፋዊ መግለጫ የነዳጅ አቅርቦት ወደ ቀድሞ ሁኔታው መመለሱን አረጋግጧል፡፡
በዚህም ምክንያት ቀደም ሲል በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ታይተው የነበሩ የአገልግሎት መስተጓጎሎች ሙሉ በሙሉ መፈታታቸው ታውቋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች የሚገኙ የዘርፉ አመራሮች እና የሚመለከታቸው አካላት የትራንስፖርት አገልግሎቱ ያለምንም ችግር እንዲቀጥልና የተቀመጠው የዋጋ ተመን ብቻ ተግባራዊ እንዲሆን በጋራ ግብረኃይል ጥብቅ ክትትል እንዲያደርጉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡
መንግስት የህዝቡን ኑሮ ለማረጋጋት እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው እንዳይስተጓጎል አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥልም ገልጿል፡፡
#ትራንስፖርት #ነዳጅ #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #የኢኮኖሚመረጋጋት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.