#Fastmereja I በኢትዮጵያ የወተትና የወተት ተዋጽኦ ምርቶች በስፋት በመታወቅ ላይ የሚገኘው ሆላንድ ዴይሪ (Holland Dairy)፤ አዲስ ያመረተውን የቫኒላ ጣዕም ያለው እርጎ በይፋ ለገበያ ማቅረቡን በዛሬዉ እለት አስታወቀ።
ይህ አዲስ የቫኒላ ጣዕም ያለው እርጎ፤ ድርጅቱ ቀደም ሲል ለገበያ ሲያቀርባቸው ከነበሩት የተፈጥሮ ፣ ማንጎ፣ ሙዝ እና ስትሮውበሪ ጣዕም ካላቸው ምርቶች በተጨማሪነት የተቀላቀለ መሆኑ ተገልጿል።
ምርቱ በጥንቃቄ ከተመረጠ ወተትና ከፍተኛ ጥራት ካላቸው ግብዓቶች የተዘጋጀ መሆኑን የገለጹት የሆላንድ ዴይሪ የንግድ ዳይሬክተር ዣን ፖል ሪዩ (Jean Paul Rieu)፤ “ትንሽ እረፍት ይውሰዱ፣ ቫኒላ ያስደስትዎታል” (Take a Pause, Vanilla Makes You Happy) በሚል መሪ ቃል የቀረበው ይህ ምርት ለተጠቃሚዎች የተለየ ጣዕምና ደስታን ለማምጣት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።
ከምርት ምርቃቱ ጋር ተያይዞ በታዋቂው ድምፃዊ እሱባለው (እሹሩሩ) የተቀናበረ አዲስ የማስታወቂያ ዜማ (Jingle) ያካተተ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ለታዳሚዎች የቀረበ ሲሆን ይህም ድርጅቱ በገበያ ውስጥ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና ወደ ደንበኞች ይበልጥ ለመቅረብ የሚያደርገውን ጥረት አካል መሆኑ ተመልክቷል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና የሚዲያ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን፤ የምርቱ የቅምሻ መርሃ-ግብርም ተካሂዷል።
ሆላንድ ዴይሪ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ስራ የጀመረ ሲሆን፤ ልዩ ልዩ የወተት ምርቶችንና የቺዝ አይነቶችን ለሀገርውስጥ ገበያ በማቅረብ ላይ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን ኩባንያው በቀጣይም የምርት አይነቶቹንና ጥራቱን በማሳደግ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡
#ቢዝነስ



Source: FastMereja









No comments yet.