የኢትዮጵያዊው ማህበረሰባዊ ሥራ ፈጣሪ በዓለም አቀፉ የስኮል ፎረም ላይ የላቀ እውቅና አገኘ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በእንግሊዝ ኦክስፎርድ ከተማ ከሚያዝያ 13 እስከ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የዘንድሮው የስኮል ወርልድ ፎረም መጠናቀቁ ተገለጠ።

በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የአካል ጉዳተኞችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰራው የብስራት ፕሮሞሽን መስራች አቶ ገድለሚካኤል አበበ ተሳትፈዋል።

በሚሲንግ ቢሊየን ኢኒሼቲቭ አማካኝነት የተመረጡት አቶ ገድለሚካኤል በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያን ተሞክሮ በማካፈል ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ከመቶ በላይ ሀገራት የተሳተፉበትና ለማህበረሰባዊ ስራ ፈጣሪዎች እውቅና በሚሰጥበት በዚህ መድረክ ላይ አቶ ገድለሚካኤል ቴክኖሎጂ እና መገናኛ ብዙኃን ለአካል ጉዳተኞች ያላቸውን ፋይዳ የሚዳስስ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በውይይቱም ወቅት ሚዲያ የማህበረሰብን ግንዛቤ በመቅረጽ ረገድ ያለውን ሚና በማንሳት ባለፉት ሃያ ዓመታት በኢትዮጵያ ያከናወኑትን የለውጥ ስራዎች አብራርተዋል።

በተጨማሪም ቴክኖሎጂ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣው አካል ጉዳተኞች የፈጠራው ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆኑ የፈጠራው ባለቤትና ውሳኔ ሰጪ መሆን ሲችሉ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ በአካል ጉዳተኝነት እና በማህበረሰባዊ ስራ ፈጠራ ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ከተመረጡ ስምንት የዓለም ተሳታፊዎች መካከል አቶ ገድለሚካኤል አንዱ በመሆን የላቀ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የስኮል ወርልድ ፎረም እ.ኤ.አ ከ2004 ጀምሮ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን በጄፍ ስኮል በተመሰረተው ስኮል ፋውንዴሽን አማካኝነት የሚዘጋጅ ነው።

ይህ መድረክ እንደ ኮፊ አናን እና ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ ያሉ ታላላቅ የዓለም መሪዎች ሀሳባቸውን ያጋሩበት ትልቅ መድረክ እንደሆነ ይታወቃል።

#SkollWorldForum #Inclusion #SocialEntrepreneurship #DisabilityRights #Technology #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2