መንግስት ለነዳጅ በወር 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረገ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

- Advertisement -
Sidebar AD

ባለፉት ወራት ያጋጠመውን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ችግር ለመፍታት መንግስት በወር 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረገ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት አየር መንገዶች በረራዎቻቸውን እየቀነሱ ሲሆን፥ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ በረራ እንደሚያቆሙ እየገለጹ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ እንዳላቋረጠ እንዲሁም የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዳልቆመ ገልጸው፥ ነገር ግን አንድም ኢትዮጵያዊ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ ሲጠይቅ አልተስተዋለም ብለዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት ገደማ ለነዳጅ ተጨማሪ ወጪ 100 ፐርሰንት ድጎማ መደረጉን ገልጸው፥ በዚህም በወር እስከ 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረግን እንገኛለን ነው ያሉት፡፡

FBC


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: