ሰሞኑን ሶሻል ሚዲያ ላይ እምብዛም ባይሆን አነጋጋሪ ከነበሩት ነገሮች አንዱ ልጃችሁን ለልጃችን የሚባልበትን “የሽምግልና” ስርአ

- Advertisement -
Sidebar AD

ሰሞኑን ሶሻል ሚዲያ ላይ እምብዛም ባይሆን አነጋጋሪ ከነበሩት ነገሮች አንዱ ልጃችሁን ለልጃችን የሚባልበትን “የሽምግልና” ስርአት የተመለከተ ነው። እና ብዙ ሰዎች አሁን ባለው የሽምግልና ስርአት ደስተኛ አይደሉም፣ ባህላችን ተበረዟልም ይላሉ።

እንደውም አንዲት ቲክቶክ ላይ የምትታወቅ ጎልማሳ ሴት ቃል በቃልም ባይሆን ምን ስትል ሰማኋት..

“አሁን ያለው የሽምግልና ስርአት በጣም ባህላችንን የጣሰ ነው። እኔ በጣም ብዙ ሀገር ዞርያለሁ አይቻለሁ ስለኛ ሀገር ባህልም ሳወራ ከማወራቸው ነገሮች አንዱ ስለሽምግልና ባህላችንም ጭምር ነው። አሁን እየተደረገ ያለው ነገር ግን ባህላችን አይደለም። ለሽምግልና የሚመጣውን ቤት የሚያክል #አበባ..ሰርግ የሚያስንቅ ድግስ ምናምን ስናይ ሴቷን በገንዘብ የመግዛት(ቤተሰቧቿ የመሸጥ) ያህል ነው” እንደዛ አይነት የሚል ሀሳብ አንስታለች።

በግሌ ምናልባት ተጥሷል ከሚባለው ባህል ትክክል ነው ብዬ የማስበው ልክ እንደ ሰርግ ቀን ለሽምግልና ቀን ባልየው መጥቶ አብሮ የሚውለው፣ የሚጨፍረው ፕሮግራሙን የሚካፈለው ነገር ነው። ከዛ ባለፈ ግን ሰው afford ማድረግ እስከቻለና አቅሙ እስካለው ድረስ የቱንም ያህል ወጪ አውጥቶ ፕሮግራሙን ደመቅ አድርጎ ሽምግልና ቢልክ ምንድነው ችግሩ? በዛ ደረጃስ የሚያወቃቅስ ነው?

ወጣቷ የህግ ባለሙያ እና አንቂ እለኒ ጎንፋ


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1