እስካሁን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን መወሰን የሚችለው ቦርድ ወደ ሥራ አለመግባቱ ተገለጸ
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን ለመወሰን የሚያስችል ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ገልጿል።
የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ የዝቅተኛ ደመወዝ ወለልን ለመወሰን የሚያስችለው ቦርድ እስካሁን ሥራ አለመጀመሩን ገልጸዋል። ቦርዱ ሥራ ያልጀመረው አሠራሩን የሚደነግገው ደንብ እስካሁን ባለመውጣቱ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት ሰነዱ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወጥቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የቀረበ ሲሆን፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን አብራርተዋል።
ደንቡ ጸድቆ ሲወጣ ቦርዱ በይፋ የሚቋቋም ሲሆን፣ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታና የገበያ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ ዝቅተኛው የደመወዝ ወለል ምን ያህል መሆን እንዳለበት ይወስናል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ በበኩላቸው፣ ደንቡን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማፅደቅ ወደ ሥራ ማስገባት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል። በሚኒስቴሩ በኩልም እየተዘጋጁ ያሉ የሕግ ማዕቀፎች መኖራቸውን አስረድተዋል። ይሁን እንጂ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለሉን ማስቀመጥ ብቻውን መፍትሔ እንደማይሆንም ገልጸዋል።
የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲኖር ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ተካቶ መውጣቱ ይታወሳል።
@seledadotio

No comments yet.