የትራምፕና የፑቲን የ90 ደቂቃ የስልክ ወግ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopian | ​የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ለ90 ደቂቃ የቆየ ሰፊ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የክሬምሊን የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ አረጋገጡ። በመሪዎቹ ውይይት ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እና የዩክሬን ወቅታዊ ሁኔታ ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳዎች ነበሩ።

​ቭላድሚር ፑቲን በውይይቱ ወቅት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲራዘም ላደረጉት ጥረት አድናቆታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ጦርነቱ ያስከተለውን ሰብአዊና ፖለቲካዊ ቀውስ በተመለከተም መክረዋል።

ምንም እንኳን ሩሲያ በዲፕሎማሲው ረገድ ከኢራን ጎን መቆሟን ብታሳውቅም፣ የምዕራባውያን የስለላ ተቋማት ግን ሞስኮ ለቴህራን የስለላና የድሮን ድጋፍ በማድረግ አሜሪካን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ ታግዛለች የሚል ጥርጣሬ አላቸው

​ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ስለ ውይይቱ በሰጡት ማብራሪያ፣ ከፑቲን ጋር ውጤታማ ቆይታ ማድረጋቸውንና መሪውን ለረጅም ጊዜ እንደሚያውቋቸው ገልጸዋል።

ፑቲን የኢራን የተቀበረ ዩራኒየም ወደ ሞስኮ እንዲዛወር ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት ማሳየታቸውን የጠቀሱት ትራምፕ፣ እርሳቸው ግን የሩሲያው መሪ ትኩረቱን በዩክሬን ያለውን ጦርነት በአፋጣኝ በማቆም ላይ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ መስጠታቸውን ተናግረዋል።

​በመጨረሻም ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት የሚቋጭበት ጊዜ እጅግ መቅረቡን በመጠቆም ለቀጣናው ሰላም ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#DonaldTrump #VladimirPutin #RussiaUkraineWar #MiddleEastConflict #USRussiaRelations #GlobalPolitics #Geopolitics #IranCeasefire


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: