🙏
አባቱን ገና በልጅነቱ ቢሞትበትም ሌላ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ በጦር ኃይል አሰልጠኖ አሳድጎታል፡፡ የስሙ ትርጓሜ “ኮከብ ብሩህ፣ ፀሐይ” ማለት ነው፡፡ ፍልስጤም ውስጥ ልዩ ስሟ “ልዳ” በምትባል ቦታ በ277 ዓ.ም ጥር 20 ተወለደ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ፡፡ ያሳደገው መስፍን ሲሞትም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ከተማ ሄደ፡፡ በዚያም የሚመለክና ሴት ልጆቻቸውን የሚገብሩለትን ደራጎን ገድሎ ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መለሳቸው፡፡ የአባቱን ሹመት ለማግኘት ወደ ፋርስም ሲሔድ ንጉሱ ዱድያኖስ ከሰባ ነገሥታት ጋር ጣዖታት ሲያመልኩ ቢያገኛቸው በፊታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ ሰማዕቱ ከመኳንንት ወገን መሆኑን የተረዳው ዱዲያኖስ አጵሎንን ብታመልክ እሾምሃለው አለው፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስም “አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ላንተ ሹመት ስል አልክደውም” አለው፡፡ ዱድያኖስም እጅግ ተቆጥቶ ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰበት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ግን ጌታችንን “” በማለት ለመነው፡፡ እግዚአብሔርም ጽናትን ሰጥቶታል፡፡ የደረሱበት እጅግ አሠቃቂ መከራዎች የሰው ኅሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው፡፡ በእንጨት ላይ ሰቅለው ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምተው ሂድ አሉት፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል፡፡ ሰውነቱን በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ሲነሰንስበት ሥጋው መሬት ላይ ወደቀ፡፡
በሰባ ችንካሮች አስቸንክሮ፣ በእሳት አስተኩሶ፣ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ፣ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ ፈወሰው፤ ኃይልና ብርታትንም ሰጠው፡፡ በመከራው ብዛት ሦስት ጊዜ ሲሞት ጌታችን ሦስት ጊዜ ከሞት አስነሣው፡፡ ለሰባት ዓመታት ከተጋደለ በኋላም ሚያዝያ 23 በሰይፍ አንገቱን ተመቶ ሲሞት ሰባውን ነገስታት አጥፍቷቸዋል፡፡ ዓለምን የናቁ ገዳማውያን ይህን አብነት አድርገው ይጸናሉ በገድልም ይተጋሉ፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
Source: FastMereja









No comments yet.