በምሥራቅ ጉራጌ ዞን አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ!በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ አራ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በምሥራቅ ጉራጌ ዞን አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ አምስት ሰዎች በታጣቂች ተገደሉ።ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ትናንት ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ በተኙበት ገብተው መሣሪያ በመተኮስ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሟች ዘመዶች ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡
ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳ ኢንሴኖ በተባለ ከተማ ውስጥ መሆኑን ለዶቼ ቬለ የተናገሩ አንድ የሟች የቅርብ ዘመድ «ታጣቂዎቹ በተለምዶ አየር ጤና ተብሎ በሚጠራው መንደር እየተኮሱ ነው የገቡት፡፡ወደ መኖሪያ ቤት በመግባት አምስት ሰዎችን ተኩሰው ከገደሉ በኋላ ተመልሰው ሄደዋል፡፡ከሟቾቹ መካከል አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ እናት ከሦስት ልጆቿ ጋር ነው» ብለዋል ፡፡
በከተማው ነዋሪ የሆኑ ሌላ የዐይን አማኝ በበኩላቸው ግድያው መፈጸሙን አረጋግጠው ጥቃት አድራሾቹ በአካባቢው በሽፍትነት የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ሳይሆኑ እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡ዶቼ ቬለ ጥቃቱን በተመለከተ ለማነጋገር በስልክ ያገኛቸው የምሥራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ሰረላ መረጃውን አሰባስበው እንደሚገልጹ ቀጠሮ ይዘው ነበር፡፡ነገር ግን በቀጠሮው ሰዓት ሥልካቸው ዝግ በመሆኑ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡
Via DW
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2