ባይናንስ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ምንዛሬ ግብይቶችን ሊያቆም ነው።የክሪፕቶ ምንዛሬ ግብይት መድረክ የሆነው ባይናንስ …

- Advertisement -
Sidebar AD
ባይናንስ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ምንዛሬ ግብይቶችን ሊያቆም ነው።
የክሪፕቶ ምንዛሬ ግብይት መድረክ የሆነው ባይናንስ (🔶 Binance )፣ ከግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶችን (P2P Trading) እንደሚያቆም አስታወቀ።
ባይናንስ አፍሪካ በኤክስ ማህበራዊ ገጹ ባወጣው መረጃ፣ ውሳኔው ከሀገሪቱ ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በቅርበት ለመስራትና የኢትዮጵያን ግቦች ለመደገፍ ታሳቢ ተደርጎ የተወሰነ መሆኑን ገልጿል።
ይህ ውሳኔ ግን የተጠቃሚዎች ገንዘብ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑንና አካውንታቸውን መጠቀም እንደሚችሉ ተቋሙ አረጋግጧል።
ይህ ውሳኔ የተሰማው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ወራት በፊት በብር የሚደረጉ የክሪፕቶ (P2P) ግብይቶች ሕገ-ወጥ መሆናቸውንና የተከለከሉ መሆናቸውን በመጥቀስ ጥብቅ ማሳሰቢያ መስጠቱን ተከትሎ ነው።
ባንኩ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ በማንኛውም መድረክም ሆነ የልውውጥ ማዕከል በብር የሚደረጉ የዲጂታል ሀብት ግብይቶች ያለ ባንኩ ፈቃድ በፍጹም የተከለከሉ መሆናቸውን አስታውቆ ነበር።
እገዳው ማንኛውንም በብር የሚሰላ የክሪፕቶ ከረንሲ ልውውጥን የሚያካትት መሆኑም በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል።
ብሔራዊ ባንክ በአሁኑ ወቅት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሥርዓት ያለው የዲጂታል ፋይናንስ ተሳትፎ እንዲኖር የሚያስችል አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ከዓለም አቀፍ አቻ ተቆጣጣሪዎችና ከአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር በንቃት እየመከረ መሆኑን መግለጹም ይታወሳል።
ባይናንስ ባወጣው በዚህ  አጭር መግለጫም ሁኔታዎች ሲመቻቹ ግብይቱን በድጋሚ ለመጀመር ተስፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1