ተቀባይነት የሌለው ውሳኔ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

— ሚኬል አርቴታ በዳኝነት ውሳኔ ላይ ያለውን ቅሬታ ገለጸ

#Ethiopia | ​የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በጨዋታው ወቅት ለቡድናቸው ተሰጥቶ የነበረው የፍፁም ቅጣት ምት በቪኤአር (VAR) መሻሩን ተከትሎ የተሰማቸውን ከፍተኛ ብስጭት ገልጸዋል።

አሰልጣኙ በወቅቱ ግልጽ የሆነ ንክኪ እንደነበር በመጥቀስ፣ የዳኝነት ውሳኔው ምስሉን 13 ጊዜ ያህል ከተመለከቱ በኋላ ሊቀየር መቻሉ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

​ይህ የዳኝነት ውሳኔ የጨዋታውን አጠቃላይ መልክ የቀየረና የተሳሳተ እንደነበር አርቴታ በቁጭት የገለጹ ሲሆን፣ በውሳኔው በእጅጉ መጎዳታቸውንም አስረድተዋል።

ይሁን እንጂ አሰልጣኙ በውሳኔው ቢበሳጩም፣ አሁንም የሊጉ ጉዞ እና ውጤቱ በራሳቸው እጅ እንደሆነና ትኩረታቸውንም ወደ ቀጣዩ ጨዋታ ማዞራቸውን ጠቁመዋል።

​መድፈኞቹ ቀጣይ ጨዋታቸውን በሜዳቸውና በደጋፊዎቻቸው ፊት ከፉልሀም ጋር እንደሚያደርጉ ያስታወሱት አርቴታ፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ትኩረታቸው በዚያ ጨዋታ ላይ ድል ማስመዝገብ መሆኑን በልበ ሙሉነት ገልጸዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#Arsenal #MikelArteta #PremierLeague #VAR #Gunners #FootballNews #FulhamvsArsenal #EPL #LondonIsRed


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1