#Ethiopia | ባለፈው እሁድ በተከናወነው የለንደን ማራቶን ውድድር የሁለት ሰዓት ግድግዳን በመስበር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበው ኬንያዊው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ ወደ ሀገሩ ሲመለስ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎለታል።
በ49ኛው የለንደን ማራቶን ርቀቱን በ1 ሰዓት 59 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በማጠናቀቅ ታሪክ የለወጠው አትሌቱ ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተከናውኖለታል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አትሌቱን በቤተ መንግሥት ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን ለላቀ ስኬቱም የገንዘብና የዓይነት ሽልማቶችን አበርክተውለታል።
ፕሬዝዳንቱ ለዓለም ክብረ ወሰኑ 5 ሚሊዮን እንዲሁም ለለንደን ማራቶን ድሉ 3 ሚሊዮን በድምሩ 8 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ በስጦታ መልክ ሰጥተውታል።
ከገንዘብ ሽልማቱ ባሻገር አትሌቱ የመረጠውን ዘመናዊ መኪና እንዲያገኝና የመኪናው ሰሌዳ ቁጥርም ታሪክ በሰራበት ሰዓት ማለትም 1:59:30 በሚል እንዲሰየም ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ ይህ ውጤት በታሪክ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት ድንቅ ስኬት መሆኑን በመጥቀስ አትሌቱን አድንቀዋል።
በዚሁ የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በተመሳሳይ ከሁለት ሰዓት በታች በሆነ ፈጣን ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
#marathon #athletics #kenya #sebastiansawe #worldrecord #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.