የቤተክርስቲያን የምረቅታት ጉዞ
#Ethiopia | የምሁር ገዳመ ኢየሱስ ታሪክ በአጭሩ
በሀገራችን ከሚገኙ ቅዱሳት መካናት መካከል ምሁር የኢየሱስ ገዳም አንዱ ነው ።
በጅማ በር ወልቂጤ በኩል ከአዲስ አበባ 210 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሰባት ቤት ጉራጌ በምሁርና አክሊል ወረዳ ይገኛል ። ምሁር የኢየሱስ ገዳም የተመሰረተው ከዮዲት ዘመን /ከ840 ዓ .ም / በፊት ሲሆን በደቡብ የሀገራችን ክፍል ከሚገኙ ገዳማት አንጋፋና ጥንታዊ ገዳም ነው።
ሀገረ ምሁር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ጋር በተሰደደ ጊዜ ከባረካቸው የኢትዮዽያ ግዛቶች አንዱ መሆኑ በድርሳነ ዑራኤል ላይ ተገልጿል።
የምሁር ገዳም ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በደብርነት የተተከለው በ9 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደሆነ እንግለፅ እንጂ ቦታው የተገደመው በጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው
ከጻድቁ አባታችን ዜና ማርቆስ ገድል እንደምንረዳው አባታችን ዜና ማርቆስ በእግዚአብሔር ፍቃድ “ሑር ሀገረ ምሁር” ወደ ምሁር ሀገር ሂድ ተብለው ደመና ጠቅሰው ወደ ምሁር በመጡ ጊዜ የምሁር ሰዎች ከአምልኮተ እግዚአብሔር ርቀው በጣኦት ያመልኩ ነበር ።
አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ምሁር ባደረጉት የመጀመሪያ ሐዋሪያዊ ጉዞ በወንጌል ትምህርትና በገቢረ ተአምር የምሁርን ሰዎች ከአምልኮተ ጣኦት ወደ ቀደመ አባቶቻቸው ሃይማኖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልስው በቀናች የክርስትና ሃይማኖት እንዲፀኑ እያስተማሩ 3 አመት በምሁር ተቀምጠዋል።
ከዚህ በኋላ ጻድቅና ቅዱስ ሐዋርያው አባታችን ዜና ማርቆስ ከምሁር ወደ ሌሎቹ የጉራጌ ግዛቶችና የተለያዩ የሀገራችን አካባቢ ተዘዋውረው ወንጌልን ሲያስተምሩ ቆይተውከሁለት ዓመታት ቆይታ በኃላ በውቅቱ ከነበሩት ግብጻዊ የኢትዮዽያ ዻዻስ አባ
[30/04, 13:29] Biruk Seiyfu – Muhur Gedam: ቄርሎስ ጋር ወደ ምሁር ለሁለተኛ ጊዜ መጡ ።
አባታችን ዜና ማርቆስ በሁለተኛው ጉዛቸው ነው የምሁር ኢየሱስ ገዳምን መሀሉ ገነት ዳሩ እሳት ይሁን ብለው የገደሙት።
ምሁር የ 44ቱ ታቦታት ሀገር ተብሎ ይጠራል ።
ምሁር የ44ቱ ታቦት ሀገር ተብሎ የሚጠራው በገዳሙ ባሉት ታቦታት ነው እንጂ በሀገረ ምሁር የተተከሉት አብያተ ክርስቲያናት 44 ብቻ አይደሉም።
መጃውን ያደረሰን 👉Biruk Seifu
በገዳሙ ጉዞ ለመጓዝ
ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ይመዝገቡ
0911083713/0913383033/0911358560
Source: GetuTemesgen









No comments yet.