በአሶሳ ዞን በደረሰ የባስ መገልበጥ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በአሶሳ ዞን በመንጌ ወረዳ በደረሰ አስከፊ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፣ በ24 ተሳፋሪዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ።

​አደጋው የደረሰው ዛሬ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ገደማ ሲሆን፣ መነሻውን በሆሞሻ ወረዳ ፆሬ 6ኛ ካምፕ መገንጠያ አድርጎ ወደ ሽርቆሌ ወረዳ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 – 01220 ቤ.ጉ የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ ባስ በመንጌ ወረዳ “አቧራ ቀበሌ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቁልቁለት ላይ ሲደርስ ተገልብጧል።

​እንደ አሶሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃ ከሆነ፣ የአደጋው መንስኤ በዝርዝር እየተጣራ ቢሆንም በቅድመ ምርመራ ግን ተሽከርካሪው ከልክ በላይ ጭነት ጭኖ ይጓዝ እንደነበር ታውቋል። ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች ወደ ሕክምና ተቋማት ተወስደው እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

​ፖሊስ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ሕግን በማክበርና የጭነት ልክን በመጠበቅ የዜጎችን ሕይወት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል። የ”ፋስት መረጃ” ዝግጅት ክፍል በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1