#Ethiopia | ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዘርፉን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የያዘ አዲስ የዩ ኤች ቲ (UHT) የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ይህ አዲስ ፋብሪካ ወተትን ያለ ማቀዝቀዣ ለስድስት ወራት ያህል ጥራቱን ጠብቆ እንዲቆይ የሚያስችል ሲሆን ለአንጋፋው ሾላ ወተት የምርት አቅም ማደግና ለተጠቃሚዎች በስፋት ተደራሽ መሆን ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደተናገሩት ፋብሪካው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ከማዳኑ ባለፈ ለበርካታ ዜጎች አዲስ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል።
በተለይም በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅ የሆነው የሾላ ወተት ምርት ወደ ተለያዩ ክልሎች እንዲደርስና የወተት አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ፋብሪካው የሚሰበስበውን የወተት መጠን እንደሚጨምርም ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ጀማል አሕመድ አክለው ገልጸዋል።
በዕለቱ ጥራት ያለው የወተት ምርት ሲያቀርቡ ለቆዩ አርሶ አደሮች የተመረጡ የወተት ላሞች ዝርያ፣ የገንዘብ ሽልማትና የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
አዲሱ ፋብሪካ የሚያመርታቸው የሾላ ወተት ምርቶች፣ የተለያዩ የአይብ ዓይነቶችና አይስክሬሞች በኩዊንስ ሱፐርማርኬትና በድርጅቱ የሽያጭ ሱቆች አማካኝነት በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እንደሚቀርቡ ታውቋል።
#ሚድሮክ #ሾላወተት #ኢንቨስትመንት #ኢንዱስትሪ #ምረቃ #ኢኮኖሚ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.