በ”ላብ አደሮች” ቀን ወጣቱ የአእምሮ ውጤቱን እንዲጠቀም የሚያስችል አዲስ ፕሮግራም በክሪኤቲቭ ኪንግደም ይፋ ሆነ፤

- Advertisement -
Sidebar AD

ይህ የወጣቶች የአእምሮ ውጤት የኢትዮጵያን መፃኢ የኢኮኖሚ መሰረት መገንባት የሚችል መሆን ይገባዋልም ተብሏል።

ክሪኤቲቭ ኪንግደም ይፋ ያደረገው ይህ ፕሮግራም የወጣቶች የአእምሮ ውጤት፣ ሃገር በቀል ቴክኖሎጂዎችና የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ተጠቅሞ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፈጠራዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁነኛ የለውጥ ስነ ምህዳር መሆኑን የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ኃይሉ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያውያን ብቃት ላይ የተመሰረተ፣ ሳይንሳዊ መሠረት ያለው አዲስ ዘመን መምጣቱን ታላሚ ያደረገው ይህ ፕሮግራም ኢትዮጵያ በዓለም የቴክኖሎጂና ፈጠራ ኢኮኖሚ ላይ ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችላትም ነው ብለዋል።

አቶ ታደሰ አክለውም ዘመኑ የዋጀውን የቴክኖሎጂ አማራጭ ዋነኛ መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የአእምሮ ውጤቶቻቸውን ለራሳቸው እና ለሌሎችም ችግር ፈቺ እና የስራ ዕድልን የሚፈጥሩበት፣ ዕውቀታቸውን አደባባይ አውጥተው እንዲጠቀሙበት ያስችላል ሲሉም ገልፀዋል።

በዚህ ፕሮግራም ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እና በአምስት ዓመታት ውስጥም ሥራ የሚፈጥርበት ግብ መቀመጡን ነው የጠቆሙት።

የዚህ ፕሮግራም መጀመር የኢትዮጵያን ያልተነካ የፈጠራ አቅም ወደ አንድ ያመጣልም ብለዋል።

በተጨማሪም በብሔራዊ ደረጃ በተቀናጀ እንቅስቃሴ የስራ ፈጣሪዎችና አጋሮቻቸውን በተገቢው ሃብት ታግዞ የሚያድግና ተጽዕኖ የሚያሳድር መፍትሔዎች የማምጣት ዕድል የያዘ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ይህ ክሪኤቲቭ ኪንግደም ፕሮግራም የግለሰቦችን አቅም ለማጎልበት፣ ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከርና ለመፍጠር ብሎም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ዋነኛ ተሳታፊ በማድረግ ኢትዮጵያ የራሷን ችግር በራሷ ልጆች መፍታት ለማስቻል ታስቦ የተቀረፀ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ሃይሉ አክለውም ለፈጠራ ስራ ዋጋ የሚሰጥና የሚያበረታታ ማህበረሰብ መፍጠር የፕሮግራሙ ግብ ሲሆን ዜጎች የፈጠራ አቅማቸው ዋነኛ እሴታቸው መሆኑን እንዲረዱም በር ይከፍታል ብለዋል።

የስራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶች ለዚሁ በተዘጋጀው
https://Creativekingdom.et ዌብሳይት ላይ መረጃዎችን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በቅርቡ ይፋ በሚደረገው የፕሮግራሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ወቅት መመዝገብ እንደሚቻል ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ታደሰ ኃይሉ አስታውቀዋል።



Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: