#Ethiopia | የካታላኑ ኩራት ባርሴሎና ከዋነኛ ተቀናቃኙ ሪያል ማድሪድ ጋር ለሚያደርገው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ፣ የአሜሪካዊቷን ዝነኛ አቀንቃኝ የኦሊቭያ ሮድሪጎን (Olivia Rodrigo) አርማ የያዘ ልዩ ማልያ እንደሚጠቀም ታወቀ።
ይህ አሰራር ክለቡ ከዋና ስፖንሰሩ ስፖቲፋይ (Spotify) ጋር ባለው ስምምነት መሰረት የሚከናወን ሲሆን፣ በታላላቅ ጨዋታዎች ላይ የዓለም አቀፍ አርቲስቶችን አርማ በማልያው ላይ በማድረግ ማስተዋወቂያ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህኛው ጨዋታም የአርቲስቷን መጠሪያ የመጀመሪያ ፊደላት የያዘው “OR” የሚል አርማ በባርሴሎና ማልያ ደረት ላይ ደምቆ ይታያል።
ይህ ልዩ እትም የሆነ ማልያ ለገበያ የቀረበ ሲሆን፣ ዋጋውም እንደ ይዘቱ ከፍ ያለ ነው። መደበኛው ልዩ ማልያ በ400 ዩሮ እየተሸጠ ሲሆን፣ የአርቲስቷ ኦሪጅናል ፊርማ ያረፈበት ማልያ ደግሞ በ3,000 ዩሮ ለሽያጭ ቀርቧል።
ባርሴሎና ከዚህ ቀደም እንደ ድሬክ፣ ሮሊንግ ስቶንስ እና ካሮል ጂ ያሉ ታዋቂ አርቲስቶችን አርማ በተመሳሳይ መልኩ መጠቀሙ ይታወሳል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#FCBarcelona #ElClasico #OliviaRodrigo #Spotify #BarcaNews #FootballFashion #LaLiga #OliviaRodrigoOR #BarcaJersey
Source: GetuTemesgen









No comments yet.