አሜሪካ ጥቃት ከፈፀመችብኝ ረዥም እና ህመም የሚያስከትል የአፀፋ ምላሽ እሰጣለሁ ስትል ኢራን ዛተች ኢራን ዋሽንግተን ጥቃቱን ከ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አሜሪካ ጥቃት ከፈፀመችብኝ ረዥም እና ህመም የሚያስከትል የአፀፋ ምላሽ እሰጣለሁ ስትል ኢራን ዛተች
ኢራን ዋሽንግተን ጥቃቱን ከፈፀመችብኝ በገልፍ አካባቢ ባሉ የአሜሪካ ቦታዎች ላይ ረዥም እና የሚያሰቃዩ የአፀፋ ምላሽ እንደምትሰጥ ገልጻለች። በሆርሙዝ የባህር ዳርቻ ላይ ያላትን ይዞታ ኢራን በድጋሚ በመግለጽ የዩናይትድ ስቴትስ ጥምረት የውሃ መስመሩን ለመክፈት የያዘውን እቅድ አወሳስቦታል።
ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ከሁለት ወራት በላይ ሲያስቆጥር የውሃ መስመሩ ተዘግቷል። 20 በመቶውን የዓለም የነዳጅ እና የጋዝ አቅርቦት እንቅስቃሴን በማስተጓጎክ የአለም የኢነርጂ ዋጋ እንዲጨምር እና የኤኮኖሚ ውድቀት ስጋትን ከፍ አድርጓል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኢል ባጋይ የሆርሙዝ ባህርን መዘጋቱን በተመለከተ እንደተናገሩት በጦርነቱ ለራሳችን ጥበቃ በሚል መብታችን ነው ብለዋል።  በአለም አቀፍ ህግ መሰረት ህጋዊ እና ተቀባይነት ያለው ነው ሲሉ አክለዋል። በሌላ በኩል የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዜጎቿ ወደ ኢራን፣ ሊባኖስ እና ኢራቅ እንዳይጓዙ  ያሳሰበች ሲሆን በአሁኑ ወቅት በነዚያ ሀገራት ያሉት በአስቸኳይ ለቀው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርባለች።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: