ነገ ለሚካሄደው የዛይድ የበጎ አድራጎት የሩጫ ውድድር ዝግ የሚሆኑ የአዲስ አበባ መንገዶች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | መነሻውንና መድረሻውን በመስቀል አደባባይ የሚያደርገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ አድራጎት የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ነገ በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል።

ቀደም ሲል በዱባይ፣ ኒውዮርክ፣ ቤጂንግ እና ናይሮቢ ሲካሄድ የቆየው ይህ ታላቅ ስፖርታዊ ኩነት በመዲናችን ሲከናወን የትራፊክ ፍሰትን ለማሳለጥ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የሩጫው መስመር ከመስቀል አደባባይ ተነስቶ በለገሃር፣ በብሔራዊ ቴአትር እና በቀድሞው ኢቢሲ መብራት በኩል ዞሮ በሠንጋ ተራ፣ በሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም በቡናና ሻይ በኩል አድርጎ ፍጻሜውን በመስቀል አደባባይ ያደርጋል።

በዚህም ምክንያት ነገ ሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚከተሉት መንገዶች ዝግ ይሆናሉ፦

ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ ወይም መቅረዝ ሆስፒታል ላይ)

ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)

ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ጥላሁን አደባባይ ላይ)

ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ለገሀር መብራት ላይ)
ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ላይ)

ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ)

ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ)

በተጨማሪም ከዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሩጫ መስመሮቹ ላይ ማንኛውንም ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ ማንኛውም የፀጥታ ስጋት ወይም አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 ወይም በመደበኛ ስልክ ቁጥሮች 011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

#ዛይድሩጫ #የበጎአድራጎትሩጫ #የመንገድዝግጅት #አዲስአበባፖሊስ #ትራፊክ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: