አቶ ገብረማርያም ይርጋ ዓለም አቀፍ የክብር ሽልማት ሊሰጣቸው ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በባህል አስተዳደር፣ በኪነ ጥበብ አመራር እና በዘርፉ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱት አቶ ገብረማርያም ይርጋ የታይላንዱ APA International Professional Management Award ተሸላሚ ሊሆኑ ነው።

ግለሰቡ በፈጠራ እና በዓለም አቀፍ የባህል ልውውጥ ረገድ ላሳዩት የላቀ አፈጻጸም ይህ እውቅና እንደተሰጣቸው ተገልጿል።

አቶ ገብረማርያም ላለፉት 15 ዓመታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም በአማራ ክልል ባህልና ኪነ ጥበብ ቢሮ በምክትል ኃላፊነት ውጤታማ ስራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል።

በቅርቡ ደግሞ በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የባህልና ኪነ ጥበባት ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን ለዚህ አዲስ ዓለም አቀፍ ስኬታቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

እንኳን ደስ አልዎት!

#culture #award #arts #leadership #internationalaward #achievement #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: