የክቡር መቶ አለቃ ለማ አሰፋ የላቀ የሥራ ስኬትና የላቁ ተግባራት በቢሾፍቱ ከተማ ተዘከሩ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የግብርናና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ውስጥ ለሰላሳ ዓመታት በሳቅ መሪነትና በታታሪነት ሲሰሩ የቆዩት የክቡር መቶ አለቃ ለማ አሰፋ የሕይወት ጉዞና የሥራ ውጤቶች የሚዘከርበት መርሃ ግብር ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።

በዕለቱም የቤተሰቦቻቸውን የሥራ ቅብብሎሽ ይፋ የማድረግ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።

ባለፈው የካቲት ወር 2018 ዓም በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት መቶ አለቃ ለማ አሰፋ በ1969 ዓም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በመቀላቀል እስከ መቶ አለቃ ማዕረግ ድረስ ሀገራቸውን በታማኝነት ያገለገሉ የጦር መኮንን ነበሩ።

ከወታደራዊ ግዳጃቸው ጎን ለጎንም በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በመያዝ እውቀታቸውን ያዳበሩ አንጋፋ ሰው ነበሩ።

በግል የንግድ ዘርፍም ቀዳሚ ከሆኑት መካከል አንዱ የነበሩት እኚህ ባለሀብት በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የዶሮና የእንስሳት መኖ ማምረቻ ድርጅት ከመመስረታቸው ባሻገር አለማ ፋርምስ እና ሊዮስ የምግብ ዘይት ፋብሪካን የመሳሰሉ ግዙፍ ተቋማትን በማቋቋም በግብርናው ዘርፍ የሚታየውን የግብዓት እጥረት ለመቅረፍ ግንባር ቀደም ሆነው ሰርተዋል።

ከግማሽ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩትና በተለያዩ የሙያ ማህበራት የቦርድ አመራር በመሆን ለሀገር ኢኮኖሚ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱት መቶ አለቃ ለማ በጥረታቸውና በእውቀታቸው ለኢትዮጵያ ወጣቶች ትልቅ አርአያ ሆነው ማለፋቸው በመታሰቢያው ፕሮግራም ላይ ተገልጿል።

ክቡር አቶ አባዱላ ገመዳ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እንዲሁም ታዋቂ ባለሀብቶች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ ሊዮስ የምግብ ዘይትና አኩሪ ምርቶች ድርጅት በቢሾፍቱ ለሚገኘው የኛ ለኛው የአረጋውያን መርጃ ማዕከል የ500 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ የሟቹን በጎ አድራጊነት በግብር አሳይቷል።

#ቢሾፍቱ #አለማፋርምስ #ሊዮስዘይት #ኢንቨስትመንት #በጎአድራጎት #ኢንዱስትሪ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: