#Ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል በለንደን ደርቢ ፉልሀምን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በኤምሬትስ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ ቪክቶር ዮኬሬስ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቡካዮ ሳካ ቀሪዋን አንድ ግብ አክሏል።
ዮኬሬስ በዚህ ውጤት ከአሌክሲስ ሳንቼዝ በኋላ በክለቡ በመጀመሪያው የውድድር ዓመት 20 እና ከዚያ በላይ ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች መሆን ችሏል።
ቡካዮ ሳካ ከ11 ጨዋታዎች በኋላ በኤምሬትስ ስታዲየም ግብ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ለሌላ ግብ የሚሆን ኳስም አመቻችቶ አቀብሏል።
ይህን ተከታታይ ድል ያስመዘገበው አርሰናል ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች ካሉት ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት አስፍቷል።
በተጨማሪም አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአንድ የውድድር ጨዋታዎችን በማሸነፍ የአርሰን ቬንገርን የ39 ጨዋታዎች ክብረ ወሰን ማሻሻል ችለዋል።
በሌሎች ጨዋታዎች ኒውካስል ብራይተንን 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ብሬንትፎርድ ዌስትሃምን 3 ለ 0 ረትቷል።
ዎልቭስ ከሰንደርላንድ ጋር 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
#arsenal #premierleague #football #victory #emiratesstadium #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen









No comments yet.