በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ጀሚላ ተሰማ የተጻፈው መጽሐፍ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የፔንክራፍት ሽልማትን አሸነፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

#E | thiopia | በቴክኖሎጂ ባለሙያነታቸው እና በጀሚ ሾው አዘጋጅነታቸው የሚታወቁት እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውያንን በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያበቁ የሚገኘው የአመኒም ሶሊዩሽንስ አይቲ ትምህርት ቤት መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀሚላ ተሰማ ትልቅ ዓለም አቀፍ ስኬት አስመዝግበዋል።

ደራሲዋ ያዘጋጁት የሚዛናዊ ህይወት ጆርናል (The Balance Life Journal) በላስ ቬጋስ በተካሄደው ዘጠነኛው የደራሲያን ንባብ መርሃ ግብር ላይ የፔንክራፍት (PenCraft Award) የአመቱ ምርጥ ረዳት ያልሆነ የጥበብ ስራ (Best Book for Nonfiction Self help) ዘርፍ አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል።

ይህ የሚዛናዊ ህይወት ጆርናል በሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት የሚያደርግና ልዩ ይዘት ያለው መጽሐፍ ሲሆን ግለሰቦች ስኬታማና የተመጣጠነ ኑሮ እንዲመሩ የሚያስችሉ በሳይንሳዊ ጥናት የተደገፉ ስድስት ዋና ዋና ምሰሶዎችን አካቷል።

እነዚህም ጤና፣ መንፈሳዊነት፣ የግልና የሙያ እድገት፣ ፋይናንስ እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነቶች ናቸው።

ጆርናሉ ሰዎች የራሳቸውን ህይወት እንዲመረምሩ፣ ግልጽነት እንዲኖራቸውና ኑሯቸውን በታቀደ መልኩ እንዲመሩ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

ደራሲ ጀሚላ ተሰማ ጆርናሉ በእውነተኛ የግል ህይወት ተሞክሮ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው፣ በተለይም የህይወት ሚዛን በጠፋበት በዚህ ዘመን ለሁሉም ሰው አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ይህ ዓለም አቀፍ እውቅና የመጽሐፉን ተደራሽነት ይበልጥ የሚያሰፋው ሲሆን፣ ወደፊትም የተለያዩ ስልጠናዎችን የመስጠትና የማህበረሰብ ተሳትፎ ስራዎችን የማከናወን እቅድ መኖሩ ተጠቁሟል።

#JemilaTessema #TheBalanceLifeJournal #PenCraftAward #Literature #SelfHelpBook #EthiopianAuthor #AwardWinner #Success #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: