ቤዝ ሪል እስቴት ቤቶችን ከማስረከብ ጎን ለጎን የ1 ሚሊዮን ብር የስልጠና ጥቅል ይፋ አደረገ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja: ቤዝ ሪል እስቴት «ህልምዎን በወራት» በሚል መሪ ቃል፣ በአለም ባንክ አካባቢ በራሱ ሙሉ የፋይናንስ ወጪ ሲገነባቸው የነበሩ 32 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን በ16 ወራት ውስጥ አጠናቆ በዛሬዉ እለት ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለባለቤቶቹ አስረከበ።

ይህ ፕሮጀክት በሪል እስቴት ዘርፉ በተደጋጋሚ የሚታየውን የግንባታ መጓተት በመስበር፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቁ ልዩ እንደሚያደርገው ተገልጿል።

የቤዝ ሪል እስቴት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ጥንቅቅ ያሉ (Fully Finished) በመሆናቸው፣ ደንበኞች ቁልፍ ከተረከቡበት ቅጽበት ጀምሮ ያለምንም ተጨማሪ ወጪና እንግልት መኖር እንዲችሉ ተደርገው የተገነቡ መሆናቸዉ ነዉ የተገለፀዉ።

በመርሀ-ግብሩ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኩባንያው መስራችና ባለቤት አቶ ኡስማን ኑር ሁሴን እንደገለጹት፤ ግንባታው በኩባንያው የፋይናንስ አቅም ብቻ መጠናቀቁ ደንበኞች የዋጋ ንረትን ሳይሰጉ ቤታቸውን በወቅቱ እንዲረከቡ ማስቻሉ የተገለፀ ሲሆን“ይህ ስኬት ለደንበኞቻችን የገባነውን ቃል በተግባር ያሳየንበት ነው’ ሲሉም አክለዉ ገልፀዋል።

የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሪት ዙልፋ መሀመድ በበኩላቸው፣ ስኬቱ ለተቋሙ ትልቅ ኩራት መሆኑን ገልጸው፤ በቅርቡ በቤተል ፍርድ ቤት አካባቢ የሚገኙ ቤቶችና በመርካቶ የሚገነቡ የንግድ ሱቆች ተጠናቀው ለምረቃ እንደሚበቁ አብስረዋል፡፡

ይህ ሪል እስቴት የመኪና ማቆሚያ፣ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የ24 ሰዓት የደህንነት አገልግሎትን ጨምሮ የተሟላ መሠረተ ልማት የተካተተበት መሆኑም ተገልጿል።

ቤዝ ሪል እስቴት ከቤት ርክክቡ ጎን ለጎን፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የ1 ሚሊዮን ብር የስልጠና ጥቅል ይፋ አድርጓል።

ይህ ስልጠናም ከቢልኮር የአመራርነት ስልጠና እና ምርምር ተቋም ጋር በመተባበር ለ1ዐዐ አዲስ ተመራቂ ወጣቶች የአመራርነት ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን፣ ይህም ወጣቶች ወደ ሥራው ዓለም እንዲቀላቀሉ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተነግሯል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1