ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስተዳደር የሚያስችል ሕግ እያዘጋጀች ነውየኢራን ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሃሚድረዛ ሃጂ-ባባኢ እን…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስተዳደር የሚያስችል ሕግ እያዘጋጀች ነው
የኢራን ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሃሚድረዛ ሃጂ-ባባኢ እንደተናገሩት፥አዲሱ ሕግ የእስራኤል መርከቦች በማንኛውም ጊዜ በዚህ ወሳኝ የባሕር መስመር ላይ እንዳያልፉ ይከለክላል።
ምክትል አፈ-ጉባኤው አክለውም ፤ረቂቅ ሕጉ የጠላት አገራት መርከቦች የጦርነት ካሳ ካልከፈሉ በስተቀር በወሽመጡ በኩል እንዳያልፉ ይከለክላል ብለዋል።
ሌሎች መርከቦች ማለፍ የሚችሉትም ከኢራን ፈቃድ እና ይሁንታ ካገኙ በኋላ ብቻ ይሆናል።
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያለው የመርከቦች እንቅስቃሴ ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት ሁኔታ መመለስ እንደማይችልም ተናገረዋል ያለው አልጀዚራ ነው።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: