አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

- Advertisement -
Sidebar AD

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ የተጣለው የባህር ላይ እገዳ፣ ኢራን በሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ 4.8 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ገቢ እንድታጣ አድርጓታል።

የፔንታጎን ባለስልጣናትን የጠቀሰው የአክሲዮስ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ ካለፈው ሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው በዚህ እገዳ ምክንያት 53 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የጫኑ 31 ታንከሮች በባህር ላይ ቆመው እንዲቀሩ ተደርገዋል።

እገዳው አሜሪካ በተኩስ አቁም ድርድሮች ላይ እንደ መደራደሪያ ለመጠቀም ባሰበችው ስትራቴጂ የተጣለ ሲሆን፣ እስካሁን ከ40 በላይ መርከቦች መንገዳቸውን እንዲቀይሩ ተገደዋል።

በየብስ ላይ ያሉት የነዳጅ ማከማቻዎች አቅማቸው በመሙላቱ ኢራን ያረጁ መርከቦችን እንደ ተንሳፋፊ ማከማቻ ለመጠቀም ብትገደድም፣ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የማከማቻ ቦታው ሙሉ በሙሉ ካለቀ የነዳጅ ጉድጓዶቿን ለመዝጋት ልትገደድ እንደምትችል ተነግሯል።

አንዳንድ የኢራን መርከቦች የአሜሪካን ክትትል ለማምለጥ በፓኪስታንና ህንድ በኩል ረጅም እና ውድ መንገዶችን በመጠቀም ነዳጁን ለቻይና ለማድረስ እየሞከሩ ሲሆን፣ ፔንታጎን በበኩሉ እርምጃው ኢራን ሽብርተኝነትን ለመደገፍ የምትጠቀምበትን የገቢ ምንጭ ለመምታት የታለመና ውጤታማ ነው ብሎታል።

ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ መስመሮችን እንደ ጦር መሳሪያ የመጠቀም እንቅስቃሴ፣ ቀጠናውን ወደ “ቀዝቃዛ ጦርነት” ምዕራፍ እያሸጋገረው መሆኑን ተንታኞች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

Captal



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: