#FastMereja I ለወር ሲካሄድ የቆየውና 600 የኤ.አይ የሙዚቃ ስራዎች የቀረቡበት ውድድር በድምቀት ተጠናቀቀ።የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ከእሁድ ኤ.አይ ስቱዲዮ ጋር በመተባበር ሲያካሂዱት የቆዩት የኤ.አይ የሙዚቃ ውድድር የአሸናፊዎች ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል። በውድድሩ ላይ 600 የሙዚቃ ስራዎች ለፉክክር የቀረቡ ሲሆን፣ በዳኞች እና በህዝብ ድምፅ ተለይተው አሸናፊ ለሆኑት የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዚሁ መሠረት፦
📌 አንደኛ የወጣው ኤፍሬም አሸናፊ የ500,000 ብር፣
📌 ሁለተኛ የወጣው ኪሩቤል ታቡ የ300,000 ብር፣
📌ሦስተኛ የወጣችው ኬቲም ተስፋዬ የ200,000 ብር ሽልማት ተረክበዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ውድድሩ ቴክኖሎጂው በጥበብ ዘርፍ ያለውን አቅም ከማሳየት ባለፈ የሀገራችንን አኩሪ ታሪክ በቴክኖሎጂ ታግዞ ለመግለጽ አስችሏል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እና የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው በበኩላቸው፣ ውድድሩ የአሁኑ ትውልድ የታሪክ እውቀቱን በዘመናዊ መንገድ እንዲያሳድግ አዲስ መንገድ የከፈተ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

Source: FastMereja









No comments yet.