አቤል ብርሃኑ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተባለ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ኢትዮጵያዊው የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው ደማቅ የሽልማት ስነ-ስርዓት የሀገሩን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርጓል።

በAfrica Golden Awards 2026 መድረክ ላይ አቤል “የአመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ” (African Travel Influencer of the Year) በመባል ታላቁን ሽልማት ተቀብሏል።

​አቤል ሽልማቱን ካሸነፈ በኋላ ባስተላለፈው መልዕክት፣ ጉዞው የተጀመረው በተወለደባትና ባደገባት ዓለም ገና መሆኑን አስታውሷል።

በተጨማሪም አቤል በገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት ”ሁሌም ከጀርባዬ ሆናችሁ ለኔ ቆሞ መታየት የደከማችሁ በሙሉ በስም የማልጠቅሳችሁ ሁሉ ከልብ በመነጨ ምስጋና አመሰግናለሁ ሽልማቱ የእናንተም ጭምር ነው!! አሁንም ጉዟችን ይቀጥላል! ”ብሏል።

ጥራቱ ዝቅ ባለ “የአሮጌ ስልክ ካሜራ” ምስሎችን መቅረፅ የጀመረው ወጣት፣ ዛሬ አህጉር አቀፍ እውቅናን በመጎናጸፍ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#AfricaGoldenAwards2026 #Ethiopia #TravelInfluencer #AfricanExcellence #የወይኗልጅ #ኢትዮጵያ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: