ከ6 ዓመታት በኋላ በግብፅ እና በሱዳን መካከል ያለው የዓባይ ወንዝ ትራንስፖርት ሊጀመር ነው
በግብፅ እና በሱዳን መካከል ለስድስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የዓባይ ወንዝ የውኃ ላይ ትራንስፖርት በቅርቡ በይፋ እንደሚጀመር ተገለጸ።አገልግሎቱ ተቋርጦ የቆየው የወንዙ የውኃ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ እና የወደብ እድሳት ሥራዎች ሲከናወኑ በመቆየታቸው ነው።
የሁለቱ አገራት ባለሥልጣናት እንደገለጹት፣ አሁን ላይ መርከቦቹ ለጉዞ ዝግጁ ናቸው። በትራንስፖርት መስመሩ ላይ የሚታዩ ቀሪ እንቅፋቶችን ለማስወገድ እና የሁለቱን አገራት የንግድና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማቀላጠፍ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
ይህ የትራንስፖርት መስመር መጀመር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሸቀጦች ልውውጥ ከማሳደጉም በላይ፣ ለቀጠናው የኢኮኖሚ ትስስር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.