የአፍሪካው ቁንጮ አሊኮ ዳንጎቴ አልተቻሉም

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአህጉራችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ፣ በፈረንጆቹ 2026 ዓመት አስገራሚ የሀብት እድገት በማስመዝገብ ግስጋሴያቸውን ቀጥለዋል።

እንደ ብሉምበርግ የቢሊየነሮች መረጃ መሠረት፣ የባለሀብቱ ጠቅላላ የሀብት መጠን 34.0 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም በዓለም የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ ወደ 69ኛ ደረጃ ከፍ እንዲሉ አድርጓቸዋል።

​ዳንጎቴ በዚህ ዓመት ብቻ 3.99 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ማግኘት የቻሉ ሲሆን፣ ይህም በአህጉሪቱ ያላቸውን የበላይነት ይበልጥ አጠናክሮታል።

​የዚህ የሀብት ዝላይ አንዱ ተጠቃሽ ምክንያት በሌጎስ የሚገኘው ግዙፉ የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ስራውን በሙሉ አቅሙ መጀመሩ ነው። ማጣሪያው በቀን 650,000 በርሜል የማምረት አቅሙን መጠቀም የጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጥታ የጄት ነዳጅ አቅርቦት መጀመሩ ተረጋግጧል።

​ይህ ስምምነት ለአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድ የኢነርጂ ዋስትናን የሚሰጥ ሲሆን፣ በተለይም በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ በሚታየው የአቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ለነዳጅ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ለመሙላት እንደ ትልቅ ዕድል ተቆጥሯል። ማጣሪያው የጄት ነዳጅ ኤክስፖርቱን በቀን ወደ 158,000 በርሜል አሳድጓል።

​በአፍሪካ የኢንዱስትሪ ባለቤትነት እና በንግድ ትስስር ረገድ ይህ የዳንጎቴ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋርነት አዲስ ምዕራፍ እንደሆነ ይታመናል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#CapitalNews ​#AlikoDangote #EthiopianAirlines #AfricaEconomy #BusinessNews #DangoteRefinery #Aviation #Ethiopia #Nigeria #WealthReport


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: