​ ሩሲያ የሶሪያ ዋና የነዳጅ አቅራቢ በመሆን ኢራንን ተካች​በሶሪያ የአሳድ መንግስት መውደቁን ተከትሎ፣ ሩሲያ ለሀገሪቱ የምታቀ…

- Advertisement -
Sidebar AD
🚨 ሩሲያ የሶሪያ ዋና የነዳጅ አቅራቢ በመሆን ኢራንን ተካች
​በሶሪያ የአሳድ መንግስት መውደቁን ተከትሎ፣ ሩሲያ ለሀገሪቱ የምታቀርበው የነዳጅ መጠን በ75 በመቶ በመጨመር የኢራንን ቦታ መረከቧን ሮይተርስ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት ሩሲያ በቀን በአማካይ 60,000 በርሜል ነዳጅ ለሶሪያ እያቀረበች ሲሆን፣ ይህም የሀገሪቱን ሲሶ (1/3) የኢነርጂ ፍላጎት ይሸፍናል።
🔹  ሶሪያ በቀን እስከ 150,000 በርሜል ነዳጅ የሚያስፈልጋት ቢሆንም፣ በሀገር ውስጥ ማምረት የምትችለው 35,000 በርሜል ብቻ በመሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ በገቢ ነዳጅ ላይ ጥገኝ ነች።ምንም እንኳን አዲሱ የደማስቆ መንግስት ወደ ምዕራባውያን እያዘነበለ ቢሆንም፣ የሀገሪቱ ደካማ ኢኮኖሚ ለጊዜው በሩሲያ ነዳጅ ላይ እንዲመሰረት አድርጎታል። ሶሪያ ከቱርክ ጋር የነዳጅ ስምምነት ለማድረግ ብትሞክርም እስካሁን ስኬታማ አልሆነችም።
ሩሲያ ይህን ነዳጅ ለሶሪያ የምታቀርበው ማዕቀብ የተጣለባቸውን መርከቦች በመጠቀም እንደሆነም ዘገባው አመልክቷል።​ይህ እርምጃ ሩሲያ በአዲሲቷ ሶሪያ ውስጥ ያላትን ተጽዕኖ ለማስቀጠል የምታደርገው የስትራቴጂ አካል ተደርጎ ተወስዷል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1