በአመራር ጥበብ እና በሰላም ግንባታ ላይ የሚያተኩረው የ’CIRCLE’ ተቋም በይፋ ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I በአንጋፋው መሪ ፓስተር ጻድቁ አብዶ የተመሰረተውና በባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ተግባቦት እንዲሁም በአመራር ብቃት ላይ የሚያተኩረው CIRCLE (Center for Intercultural, Religious, Communication, Leadership Excellence) የተሰኘው ተቋም የምረቃ ስነ-ስርዓቱን አከናውኗል። ተቋሙ በዋናነት በአመራር ጥራት፣ በሰላምና እርቅ እንዲሁም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተገልጿል።

በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተቋሙ ራዕይ ለተሳታፊዎች ቀርቧል። የክብር እንግዶቹ ባደረጉት ንግግር፣ የዚህ መሰል ተቋም መመስረት ለሀገር ሰላምና ለመሪዎች የአቅም ግንባታ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የCIRCLE መስራች ፓስተር ጻድቁ አብዶ በአገልግሎት ዘርፍ ከ50 ዓመታት በላይ፣ በአመራርነት ደግሞ ከ40 ዓመታት በላይ ያካበቱትን ሰፊ ልምድ ወደ ተቋማዊ አሰራር በመቀየር ለትውልድ ለማስተላለፍ አልመው የተነሱ መሆኑ ተመላክቷል። ተቋሙ በተለይ የተለያዩ ባህሎችና እምነቶች ባሏቸው ማህበረሰቦች መካከል ውጤታማ ተግባቦትና የአመራር ልህቀት እንዲሰፍን በትጋት እንደሚሰራ ታውቋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2