አብዲ ሀሰን እና ቃልዓብ ወርቁ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ/ም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ኢሰመኮ አካባቢ ነው የስርቆት ወንጀሉን የፈጸሙት።
ኢብራሂም ሀሰን የተባሉ የዩናይትድ አረብ ኢምሬት ዜግነት ያላቸው የግል ተበዳይ በአካባቢው ካለ ሱፐር ማርኬት ዕቃ ገዝተው ወደ አረፉበት ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል እያመሩ ሳለ ተጠርጣሪዎቹ በግራና በቀኝ ሆነው በማዋከብ አንደኛው ተጠርጣሪ ሄድ ፎን ግዛን ሲል ሁለተኛው ተጠርጣሪ ከግል ተበዳይ ኪስ ውስጥ በመግባት ግምቱ 2 መቶ ሺ ብር የሚያወጣ አይፎን15 ፕሮማክስ ሞባይል ስልክ በማውጣት ከአካባቢው መሰወራቸውን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የባምቢስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።
ፖሊስ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ፈጣን የሆነ የምርመራ እና የክትትል ስራ በመስራት ሁለቱንም ተጠርጣሪዎች በሰዓታት ልዩነት ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው መቻሉን አስታውቋል።
ራስን ባልተገባ መንገድ ለማበልጸግ መሠል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚገቡ አካላት ከፖሊስ አይን እና ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ አውቀው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
Addis Ababa police

Source: Yeneta Tube









No comments yet.