የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የሀብት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ
የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ በሀብታቸው ላይ ከፍተኛ እድገት ማስመዝገባቸው ተሰማ።
እንደ ብሉምበርግ የቢሊየነሮች መረጃ መሠረት፣ የዳንጎቴ ጠቅላላ የሀብት መጠን ወደ 34.0 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል።
ይህ የሀብት ዝላይ በፈረንጆቹ 2026 ዓመት ውስጥ ብቻ 3.99 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ እንዲያገኙ ያስቻላቸው ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥም ወደ 69ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጡ አድርጓቸዋል።
ምንም እንኳን ሌሎች አፍሪካውያን ቢሊየነሮች በዓመቱ ውስጥ ያስመዘገቡት የትርፍ ዕድገት መጠን ከእሳቸው ቢበልጥም፣ ዳንጎቴ አሁንም የአህጉሪቱን ቀዳሚነት በሰፊ ልዩነት እንደያዙ ቀጥለዋል።
ከዚህ የሀብት እድገት ጋር ተያይዞ በሌጎስ የሚገኘው የናይጄሪያው ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጥታ የጄት ነዳጅ አቅርቦት መጀመሩ የተዘገበ ሲሆን፣ ይህም ከአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድ ጋር ያለውን የኢነርጂ ትስስር አጠናክሮታል።
ማጣሪያው በቀን 650,000 በርሜል የማምረት ሙሉ አቅሙን እየተጠቀመ ሲሆን፣ የጄት ነዳጅ ኤክስፖርትም በቀን ወደ 158,000 በርሜል ከፍ ብሏል። በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በተፈጠረው የአቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ለነዳጁ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል።(ካፒታል ኢትዮጵያ)
@seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.