በማደያዎች የሚታየው የተሽከርካሪዎች ሰልፍ ያልተቃለለው ከጅቡቲ የሚነሳው የነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ጉዞ ቀናትን ስለሚፈጅ እንደ

- Advertisement -
Sidebar AD

በማደያዎች የሚታየው የተሽከርካሪዎች ሰልፍ ያልተቃለለው ከጅቡቲ የሚነሳው የነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ጉዞ ቀናትን ስለሚፈጅ እንደሆነ ተገለጸ

መንግሥት የነዳጅ አቅርቦት ወደነበረበት መጠን እንዲመለስ ቢወስንም፣ ከጅቡቲ የሚነሱት ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት የሚያደርጉት ጉዞ ቀናትን ስለሚፈጅ በማደያዎች የሚታየውን የተሽከርካሪዎች ሰልፍ በፍጥነት ማቃለል እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር አስታውቋል።

የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ከሚያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በጅቡቲ የነዳጅ ጭነት መጀመሩን አስታውሰው፣ በቀጣይ ሳምንታት ሰልፉ እየተቃለለ በመሔድ ወደነበረበት መደበኛ ሁኔታ ይመለሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

የናፍጣ አቅርቦት፣ ወደ ቀድሞው 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ ቢወሰንም አሁን ላይ ያለው የነዳጅ ፍላጎት መናር፣ በርካታ ተሽከርካሪዎች በሰልፍ ላይ መቆየታቸው እና የተቋረጡ ፕሮጀክቶች ዳግም ስራ መጀመራቸው የተፈጠረው መጨናነቅ በአጭር ጊዜ እንዳይፈታ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ፕሬዝዳንቱ አመላክተው፤ ይህ ሁኔታ ለሳምንታት ሊቀጥል እንደሚችል ያላቸውን ግምት ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት 800 ገደማ የነዳጅ ማደያዎች እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ ኤፍሬም፣ የሚታየውን ሰልፍ ለማስቀረት ማደያዎች አገልግሎታቸውን ማቀላጠፍ እንዳለባቸው መክረዋል።
ለዚህም የነዳጅ መቅጃ ፓምፖችን ቁጥር መጨመርና ሌሎች የአሰራር ማሻሻያዎችን መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል።

#አሐዱ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: