“በአደባባይና በጎዳና ላይ የሚካሄድ የሃይማኖት ስብከት ይቁም” – ጉባኤው
የመቐለ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 26/2018 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በአደባባይና ጎዳና ላይ የሚካሄድ የሃይማኖት ስብከት እንዲቆም አሳስቧል።
ጉባኤው በመቐለ አደባባዮችና ጎዳናዎች ከተለመደው ባፈነገጠ መልኩ በድምፅ ማጉያ የተደገፉ የሃይማኖት ስብከቶች እየታዩ መሆኑን ጠቅሶ፤ ተፈናቃዮች ቀያቸውን ለቀው በስቃይ ባሉበትና ህዝቡ በከባድ ችግር ውስጥ በተዘፈቀበት ሁኔታ በሃይማኖት ሽፋን ሰላም የሚያውኩ አካላት አደብ መግዛት እንዳለባቸው በአፅንኦት ገልጿል።
ህዝብ እና ተሸከርካሪዎች በብዛት በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ከህዝብ ፈቃድ ውጪ በድምፅ ማጉያ የሚካሄድ ስብከት መቆም እንዳለበት አሳስቧል።
በተለያዩ አማኞች መኖሪያና የአምልኮ ቦታዎች ድንጋይ የመወርወር፣ በመጥፎ ቃላት የማንቋሸሽና አካል የማጉደል ተግባራት እንዳሉና ይህን ከጅምሩ ሥርዓት ማስያዝ እንደሚገባ አሳስቧል።
ማንኛውም ሰው በሚከተለው ሃይማኖት ምክንያት ለስድብና አካል ጉዳት መዳረግ ሃይማኖት የሚፃረር ተግባር በመሆኑ አንዱ የሌላውን ክብርና እሴት ከሚጎዳ ስብከት መቆጠብ እንዳለበትና ህዝቡ ካለበት ተደራራቢ ፈተና አንጻር በሃይማኖት ሽፋን ሌላ መከራ መጋበዝ እንደማይገባ መክሯል።
ይህ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፣ የእስልምና ፣ የካቶሊክና የወንጌላውያን አማኞች በጋራ ያቋቋሙት ነው።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.