ኢራን ለአሜሪካ የባህር ኃይል ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠች፤ በሆርሙዝ ስትሬት ያለው ውጥረት አይሏል
“ከቀጠናው ራቁ!” — ኢራን
ዶናልድ ትራምፕ “አሜሪካ በባህር ላይ ለተቀረቀሩ መርከቦች እርዳታ ታደርጋለች” ማለታቸውን ተከትሎ፣ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት የአሜሪካ የባህር ኃይል ከሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ እንዲርቅ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ኢራን በማስጠንቀቂያዋ ላይ ማንኛውም የአሜሪካ የጦር መርከብ ወደ ቀጠናው መጠጋት “ለማይፈለግ ግጭት መንስኤ ሊሆን ይችላል” ስትል ገልጻለች።
ይህ ማስጠንቀቂያ የመጣው ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ በዓለም አቀፍ የውሃ አካላት ላይ ለሚስተጓጎሉ የንግድ መርከቦች ጥበቃና ድጋፍ እንደምታደርግ በይፋ ከተናገሩ በኋላ ነው። ሆርሙዝ ለዓለም የነዳጅ ንግድ ቁልፍ መተላለፊያ እንደመሆኑ፣ አሁን የታየው የቃላት ጦርነት በነዳጅ ገበያውና በቀጠናው ሰላም ላይ ስጋት ደቅኗል።
የኢራን የባህር ኃይል በቀጠናው ያለውን እንቅስቃሴ በቅርብ እንደሚከታተልና “ሉዓላዊነቴን የሚጋፋ ማንኛውንም እንቅስቃሴ አልታገስም” ማለቷ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ወደ ከፋ ደረጃ አድርሶታል። በአሁኑ ወቅት በባህር ወሽመጡ አካባቢ ያለው ወታደራዊ ዝግጅት ከፍተኛ መሆኑ ተዘግቧል።
@seledadotio

No comments yet.