#Ethiopia | የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ በቤት ልማት ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችለውን ታሪካዊ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
ይህ ስምምነት የተደረገው በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መሪዎች መካከል የተደረሰውን የጋራ ልማት ትብብር መነሻ በማድረግ ሲሆን በኮርፖሬሽኑ እና በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት መካከል የተፈጸመ ነው።
ስምምነቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ረሻድ ከማል እና የማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ኢማኑኤል አዲል በጁባ ከተማ በጋራ ፈርመዋል።
ውሉ ኮርፖሬሽኑ ያለውን የቴክኒክ ብቃት እና የዳበረ ልምድ ተጠቅሞ በጁባ ዘመናዊ መኖሪያዎችን፣ የንግድ ማዕከላትንና የመንግሥት ቢሮዎችን እንዲገነባ ዕድል ይሰጣል።
ዶክተር ረሻድ ከማል እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ በምሥራቅ አፍሪካና በመላው አህጉሪቱ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ ባቀደው መሠረት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተሸጋግሯል።
የማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ኢማኑኤል አዲል በበኩላቸው የኢትዮጵያ የከተሞች ዕድገትና የቤት ልማት ተሞክሮ ለአፍሪካውያን አርአያ መሆኑን ጠቅሰው ይህን ተሞክሮ በጁባ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ይህ ትብብር የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ትስስር ከማጠናከሩ ባሻገር በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት ያስችላል።
የስምምነቱን አፈጻጸም የሚከታተልና ዝርዝር የፕሮጀክት ሰነዶችን የሚያዘጋጅ የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ እንዲቋቋምም መግባባት ላይ ተደርሷል።
#ደቡብሱዳን #ቤትልማት #ኮንስትራክሽን #ኢኮኖሚ #አፍሪካ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.